Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




1 ነገሥት 12:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 ንጉ​ሡም ሮብ​ዓም አስ​ገ​ባ​ሪ​ውን አዶኒ​ራ​ምን ላከ፤ እስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ በድ​ን​ጋይ ደበ​ደ​ቡት፥ ሞተም። ንጉ​ሡም ሮብ​ዓም ፈጥኖ ወደ ሰረ​ገ​ላው ወጣ፤ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ሸሸ።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 ንጉሥ ሮብዓም የጕልበት ሠራተኞች አለቃ የነበረውን አዶኒራምን ላከው፤ ነገር ግን እስራኤል ሁሉ በድንጋይ ወግረው ገደሉት። ንጉሡ ሮብዓም ግን እንደ ምንም ብሎ ሠረገላው ላይ በመውጣት ወደ ኢየሩሳሌም ሸሸ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 ከዚህም በኋላ ንጉሥ ሮብዓም የግዳጅ ሥራ ኀላፊ የነበረውን አዶኒራምን ወደ እስራኤላውያን እንዲሄድ ላከው፤ እነርሱ ግን በድንጋይ ወግረው ገደሉት፤ በዚህን ጊዜ ሮብዓም በፍጥነት ወደ ሠረገላው ገብቶ ወደ ኢየሩሳሌም በመሄድ አመለጠ።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 ከዚህም በኋላ ንጉሥ ሮብዓም የግዳጅ ሥራ ኀላፊ የነበረውን አዶኒራምን ወደ እስራኤላውያን እንዲሄድ ላከው፤ እነርሱ ግን በድንጋይ ወግረው ገደሉት፤ በዚህን ጊዜ ሮብዓም በፍጥነት ወደ ሠረገላው ገብቶ ወደ ኢየሩሳሌም በመሄድ አመለጠ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 ንጉሡም ሮብዓም አስገባሪውን አዶኒራምን ሰደደ፤ እስራኤልም ሁሉ በድንጋይ ደበደቡት፤ ሞተም። ንጉሡም ሮብዓም ፈጥኖ ወደ ሠረገላው ወጣ ወደ ኢየሩሳሌምም ሸሸ።

Ver Capítulo Cópia de




1 ነገሥት 12:18
12 Referências Cruzadas  

አዶ​ኔ​ራ​ምም ግብር አስ​ገ​ባሪ ነበረ፤ የአ​ኪ​ሎ​ትም ልጅ ኢዮ​ሳ​ፍጥ ታሪክ ጸሓፊ ነበረ፤


አኪ​ያ​ልም የቤት አዛዥ፥ ኤል​ያ​ቅም የቤት አዛ​ዦች አለቃ ነበረ፥ የሳ​ፋን ልጅ ኤል​ያ​ፍም የቤተ ሰብ ሐላፊ፥ የአ​ዶን ልጅ አዶኒ​ራ​ምም ግብር አስ​ገ​ባሪ ነበረ።


በየ​ወ​ሩም እያ​ፈ​ራ​ረቀ ወደ ሊባ​ኖስ ዐሥር ዐሥር ሺህ ይልክ ነበር፤ አንድ ወርም በሊ​ባ​ኖስ፥ ሁለት ወርም በቤ​ታ​ቸው ይቀ​መጡ ነበር። አዶ​ኒ​ራ​ምም የገ​ባ​ሪ​ዎች አለቃ ነበረ።


ንጉ​ሡም ሮብ​ዓም አስ​ገ​ባ​ሪ​ውን አዶ​ራ​ምን ወደ እነ​ርሱ ላከው፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች በድ​ን​ጋይ ወገ​ሩት፤ ሞተም፤ ንጉ​ሡም ሮብ​ዓም ፈጥኖ ወደ ሰረ​ገ​ላው ወጣ፤ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ሸሸ።


ወደ እር​ሱም ሮጡ በን​ጉ​ሡም ትእ​ዛዝ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት አደ​ባ​ባይ ውስጥ በድ​ን​ጋይ ደበ​ደ​ቡት።


ሙሴም፦ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጮኸ፤ እን​ዲ​ህም አለ፥ “ለዚህ ሕዝብ ምን ላድ​ርግ? በድ​ን​ጋይ ሊወ​ግ​ሩኝ ጥቂት ቀር​ቶ​አ​ቸ​ዋ​ልና።”


ልበ ሙሉው ኀይ​ለ​ኛም በኀ​ይሉ አይ​ተ​ማ​መ​ንም፤ ነገር ግን በዚያ ቀን ዕራ​ቁ​ቱን ሆኖ ይሸ​ሻል” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


ማኅ​በሩ ሁሉ ግን “በድ​ን​ጋይ እን​ው​ገ​ራ​ቸው” አሉ። የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ክብር ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ሁሉ በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ተገ​ለጠ።


ከዚ​ህም በኋላ የቤተ መቅ​ደሱ ሹም ከሎ​ሌ​ዎቹ ጋር ሔዶ አባ​ብሎ አመ​ጣ​ቸው፤ በግ​ድም አይ​ደ​ለም፤ በድ​ን​ጋይ እን​ዳ​ይ​ደ​በ​ድ​ቧ​ቸው ሕዝ​ቡን ይፈሩ ነበ​ርና።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios