Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




1 ነገሥት 10:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 እኔም መጥቼ በዐ​ይኔ እስ​ካይ ድረስ የነ​ገ​ሩ​ኝን አላ​መ​ን​ሁም ነበር ፤ እነ​ሆም፥ እኩ​ሌ​ታ​ውን አል​ነ​ገ​ሩ​ኝም ነበር፤ በሀ​ገሬ ሳለሁ ከነ​ገ​ሩኝ ይልቅ የበ​ለጠ መል​ካም ተጨ​ማሪ አየሁ።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 ይሁን እንጂ፣ መጥቼ እነዚህን ነገሮች በዐይኔ እስካይ ድረስ የተነገረኝን አላመንሁም ነበር፤ በርግጥ ግማሹ እንኳ አልተነገረኝም፤ ጥበብህና ብልጽግናህ ከሰማሁት እጅግ ይልቃል።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 ነገር ግን እዚህ ድረስ መጥቼ በዐይኔ እስካየው ድረስ የተነገረኝን ሁሉ አላመንኩም ነበር፤ በጆሮዬ የሰማሁት በዐይኔ ያየሁትን እኩሌታ እንኳ አይሆንም፤ በእርግጥም ጥበብህና ሀብትህ በአገሬ ሳለሁ ከተነገረኝ በጣም ይበልጣል።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 ነገር ግን እዚህ ድረስ መጥቼ በዐይኔ እስካየው ድረስ የተነገረኝን ሁሉ አላመንኩም ነበር፤ በጆሮዬ የሰማሁት በዐይኔ ያየሁትን እኩሌታ እንኳ አይሆንም፤ በእርግጥም ጥበብህና ሀብትህ በአገሬ ሳለሁ ከተነገረኝ በጣም ይበልጣል።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 እኔም መጥቼ በዐይኔ እስካይ ድረስ የነገሩኝን አላመንሁም ነበር፤ እነሆም፥ እኩሌታውን አልነገሩኝም ነበር፤ ጥበብህና ሥራህ ከሰማሁት ዝና ይበልጣል።

Ver Capítulo Cópia de




1 ነገሥት 10:7
9 Referências Cruzadas  

ንጉ​ሡን ሰሎ​ሞ​ን​ንም አለ​ችው፥ “ስለ ነገ​ር​ህና ስለ ጥበ​ብህ በሀ​ገሬ ሳለሁ የሰ​ማ​ሁት ዝና እው​ነት ነው።


ሚስ​ቶ​ችህ የተ​መ​ሰ​ገኑ ናቸው፤ በፊ​ትህ ሁል​ጊዜ የሚ​ቆሙ፥ ጥበ​ብ​ህን የሚ​ሰሙ እነ​ዚህ አገ​ል​ጋ​ዮ​ች​ህም ምስ​ጉ​ኖች ናቸው።


በዓ​ለም የደ​ከመ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይድ​ናል፥ ጥፋ​ትን አያ​ይ​ምና።


ከጥ​ንት ጀምሮ ይቅ​ር​ታ​ህን ለሚ​ጠ​ባ​በቁ ምሕ​ረ​ትን ከም​ታ​ደ​ር​ግ​ላ​ቸው ከአ​ንተ በቀር ሌላ አም​ላክ አላ​የ​ንም፤ አል​ሰ​ማ​ን​ምም።


በጎነቱ እንዴት ታላቅ ነው! ውበቱስ እንዴት ታላቅ ነው! እህል ጐበዛዝቱን፥ ጉሽ ጠጅም ቈነጃጅቱን ያለመልማል።


እነርሱም ሕያው እንደ ሆነ ለእርስዋም እንደ ታያት ሲሰሙ አላመኑም።


ነገር ግን መጽ​ሐፍ፥ “ዐይን ያላ​የው፥ ጆሮም ያል​ሰ​ማው፥ በሰ​ውም ልቡና ያል​ታ​ሰበ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለሚ​ወ​ዱት ያዘ​ጋ​ጀው ነው።” ብሎ የለ​ምን?


ወዳጆች ሆይ፥ አሁን የእግዚአብሔር ልጆች ነን፥ ምንም እንደምንሆን ገና አልተገለጠም። ዳሩ ግን ቢገለጥ እርሱ እንዳለ እናየዋለንና እርሱን እንድንመስል እናውቃለን።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios