Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




1 ቆሮንቶስ 7:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 ለጸ​ሎት እን​ድ​ት​ተጉ ከም​ት​ስ​ማ​ሙ​በት ጊዜ ብቻ በቀር፥ ባልና ሚስት አት​ለ​ያዩ፤ ዳግ​መኛ ሰይ​ጣን ድል እን​ዳ​ያ​ደ​ር​ጋ​ችሁ በአ​ን​ድ​ነት ኑሩ፤ ሰው​ነ​ታ​ችሁ ደካማ ነውና ።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 በጸሎት ለመትጋት ተስማምታችሁ ለተወሰነ ጊዜ ካልሆነ በቀር፣ እርስ በርሳችሁ አትከላከሉ፤ ራሳችሁን ባለመግዛት ሰይጣን እንዳይፈታተናችሁ እንደ ገና ዐብራችሁ ሁኑ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 ለጸሎት ለመትጋት ተስማምታችሁ ለተወሰነ ጊዜ ካልሆነ በቀር፥ እርስ በርሳችሁ አትከላከሉ፤ እንዲሁም ራሳችሁን ስለ አለመግዛት ሰይጣን እንዳይፈታተናችሁ አብራችሁ ሁኑ።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 በጸሎት ለመትጋት ሁለታችሁም ተስማምታችሁ ለተወሰነ ጊዜ ካልሆነ በቀር በመለያየት አንዱ የሌላውን የጋብቻ መብት አይከልክል። በዚህም ምክንያት ራሳችሁን መቈጣጠር አቅቶአችሁ ሰይጣን እንዳይፈታተናችሁ እንደገና አብራችሁ ሁኑ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 ለጸሎት ትተጉ ዘንድ ተስማምታችሁ ለጊዜው ካልሆነ በቀር፥ እርስ በርሳችሁ አትከላከሉ፤ ራሳችሁን ስለ አለመግዛት ሰይጣን እንዳይፈታተናችሁ ደግሞ አብራችሁ ሁኑ።

Ver Capítulo Cópia de




1 ቆሮንቶስ 7:5
11 Referências Cruzadas  

ሕዝ​ቡ​ንም፥ “ለሦ​ስ​ተ​ኛው ቀን ተዘ​ጋጁ፤ ወደ ሴቶ​ቻ​ች​ሁም አት​ቅ​ረቡ” አለ።


ከእ​ር​ስ​ዋም ሌላ ቢያ​ገባ፥ ቀለ​ብ​ዋን፥ ልብ​ስ​ዋ​ንም፥ ለጋ​ብ​ቻ​ዋም ተገ​ቢ​ውን ይስ​ጣት፤ እን​ዳ​ል​በ​ደ​ላ​ትም ምስ​ክር ያሰ​ማ​ባት።


ሕዝ​ቡ​ንም ሰብ​ስቡ፤ ማኅ​በ​ሩ​ንም ቀድሱ፤ ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ቹ​ንም ጥሩ፤ ጡት የሚ​ጠ​ቡ​ት​ንና ሕፃ​ና​ትን ሰብ​ስቡ፤ ሙሽ​ራው ከእ​ል​ፍኙ፥ ሙሽ​ራ​ዪ​ቱም ከጫ​ጕ​ላዋ ይውጡ።


ለሠራዊት ጌታ ለእግዚአብሔር ቤት ካህናት ለነቢያትም፦ ባለፉት ዓመታት እንዳደረግሁት በአምስተኛው ወር መለየትና ማልቀስ ይገባኛልን? ብለው ይናገሩ ዘንድ ልኮአቸው ነበር።


ይህ ዐይነት ግን ከጸሎትና ከጦም በቀር አይወጣም፤” አላቸው።


እርሱ ግን “ይህ ነገር ለተሰጣቸው ነው እንጂ ለሁሉ አይደለም፤


ያን ጊዜ ኢየሱስ “ሂድ፤ አንተ ሰይጣን ‘ለጌታህ ለአምላክህ ስገድ እርሱንም ብቻ አምልክ’ ተብሎ ተጽፎአልና” አለው።


ሚስት በራ​ስዋ አካል ሥል​ጣን የላ​ትም፤ ሥል​ጣን ለባ​ልዋ ነው እንጂ፤ እን​ዲ​ሁም ባል በራሱ አካል ሥል​ጣን የለ​ውም፤ ሥል​ጣን ለሚ​ስቱ ነው እንጂ።


ስለዚህ እኔ ደግሞ ወደ ፊት እታገሥ ዘንድ ባልተቻለኝ ጊዜ “ፈታኝ ምናልባት ፈትኖአቸዋል፤ ድካማችንም ከንቱ ሆኖአል፤” ብዬ እምነታችሁን ለማወቅ ላክሁ።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios