Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




1 ቆሮንቶስ 7:30 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

30 ያለ​ቀሱ እን​ዳ​ላ​ለ​ቀሱ ይሆ​ናሉ፤ ደስ ያላ​ቸ​ውም ደስ እን​ዳ​ላ​ላ​ቸው ይሆ​ናሉ፤ የሸ​ጡም እን​ዳ​ል​ሸጡ ይሆ​ናሉ፤ የገ​ዙም እን​ዳ​ል​ገዙ ይሆ​ናሉ።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

30 የሚያለቅሱ እንደማያለቅሱ፣ ደስተኞች ደስ እንደማይላቸው ይሁኑ፤ ዕቃ የሚገዙም የገዙት ነገር የእነርሱ እንዳልሆነ ይቍጠሩ፤

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

30 የሚያለቅሱም እንደማያለቅሱ፥ ደስ የሚላቸውም ደስ እንደማይላቸው፥ የሚገዙም ምንም እንደሌላቸው፥

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

30 የሚያዝኑም እንደማያዝኑ፥ የሚደሰቱ እንደማይደሰቱ ሆነው ይኑሩ፤ ዕቃ የሚገዙ፥ ምንም ዕቃ እንደሌላቸው አድርገው ይቊጠሩ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

30 የሚያለቅሱም እንደማያለቅሱ፥ ደስ የሚላቸውም ደስ እንደማይላቸው፥

Ver Capítulo Cópia de




1 ቆሮንቶስ 7:30
14 Referências Cruzadas  

በእ​ጅህ ነፍ​ሴን አደራ እሰ​ጣ​ለሁ፤ የጽ​ድቅ አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ ተቤ​ዠኝ።


ለማ​ል​ቀስ ጊዜ አለው፥ ለመ​ሣ​ቅም ጊዜ አለው፤ ዋይ ለማ​ለት ጊዜ አለው፥ ለመ​ዝ​ፈ​ንም ጊዜ አለው።


ሞት ሰዎ​ችን ዋጠ፤ በረ​ታም፤ እንደ ገናም ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከፊት ሁሉ እን​ባን ያብ​ሳል፤ የሕ​ዝ​ቡ​ንም ስድብ ከም​ድር ሁሉ ላይ ያስ​ወ​ግ​ዳል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በአፉ ተና​ግ​ሮ​አ​ልና።


ቅዱስ ሕዝብ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ውስጥ በጽ​ዮን ይኖ​ራል፤ ልቅ​ሶን አል​ቅሺ፤ ይቅር በለ​ኝም በዪ፤ ልቅ​ሶ​ሽን ባየ ጊዜ ይቅር ይል​ሻል፤ ሰም​ቶ​ሻ​ልና።


ጊዜው መጥ​ቶ​አል፤ ቀኑ እነሆ ቀር​ቦ​አል፤ መቅ​ሠ​ፍቷ በሁ​ለ​ን​ተ​ናዋ መል​ቶ​አ​ልና የሚ​ገዛ ደስ አይ​በ​ለው፤ የሚ​ሸ​ጥም አይ​ዘን።


አብ​ር​ሃም ግን እን​ዲህ አለው፦ ‘ልጄ ሆይ፥ አንተ በሕ​ይ​ወ​ትህ ተድ​ላና ደስታ እን​ዳ​ደ​ረ​ግህ፥ አል​ዓ​ዛ​ርም እን​ዲሁ ሁል​ጊዜ በች​ጋር እንደ ነበረ ዐስብ፤ አሁን ግን እን​ዲሁ እርሱ በዚህ ፈጽሞ ተድ​ላና ደስታ ያደ​ር​ጋል፤ አንተ ግን መከራ ትቀ​በ​ላ​ለህ።


ዛሬ የም​ት​ራቡ፥ ብፁ​ዓን ናችሁ፤ ትጠ​ግ​ባ​ላ​ች​ሁና፤ ዛሬ የም​ታ​ለ​ቅሱ፥ ብፁ​ዓን ናችሁ፤ ትስ​ቃ​ላ​ች​ሁና።


ዛሬ ለም​ት​ጠ​ግቡ፥ ወዮ​ላ​ችሁ፥ ትራ​ባ​ላ​ች​ሁና፤ ዛሬ ለም​ት​ስ​ቁም ወዮ​ላ​ችሁ፥ ታዝ​ና​ላ​ች​ሁና፤ ታለ​ቅ​ሳ​ላ​ች​ሁ​ምና።


እና​ን​ተም ዛሬ ታዝ​ና​ላ​ችሁ፤ እን​ደ​ገ​ናም አያ​ች​ኋ​ለሁ፤ ልባ​ች​ሁም ደስ ይለ​ዋል፤ ደስ​ታ​ች​ሁ​ንም የሚ​ወ​ስ​ድ​ባ​ችሁ የለም።


ነገር ግን ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን እን​ዲህ ይቀ​ናል፤ የዚህ ዓለም ኑሮ ሁሉ ሊያ​ልፍ ቀር​ቦ​አ​ልና፤ አሁ​ንም ያገቡ እን​ዳ​ላ​ገቡ ይሆ​ናሉ።


የበሉ እን​ዳ​ል​በሉ ይሆ​ናሉ፤ የጠ​ጡም እን​ዳ​ል​ጠጡ ይሆ​ናሉ፤ የዚህ ዓለም ተድላ ሁሉ ያል​ፋ​ልና።


ራስዋን እንደ አከበረችና እንደ ተቀማጠለች ልክ ሥቃይና ሐዘን ስጡአት። በልብዋ ‘ንግሥት ሆኜ እቀመጣለሁ፤ ባልቴትም አልሆንም፤ ሐዘንም ከቶ አላይም፤’ ስላለች፥


በዙፋኑ መካከል ያለው በጉ እረኛቸው ይሆናልና፤ ወደ ሕይወትም ውሃ ምንጭ ይመራቸዋልና፤ እግዚአብሔርም እንባዎችን ሁሉ ከዐይናቸው ያብሳል።”


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios