Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




1 ቆሮንቶስ 6:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 እን​ግ​ዲህ ፀብና ክር​ክር ካላ​ችሁ፥ ከመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ጀምሮ ውር​ደት እን​ደ​ሚ​ሆ​ን​ባ​ችሁ ዕወቁ፤ እን​ግ​ዲ​ያማ እን​ዴት አት​ነ​ጠ​ቁም? እን​ዴ​ትስ አት​ገ​ፉም?

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 እንግዲህ በመካከላችሁ መካሰስ መኖሩ ራሱ ውድቀታችሁን ያሳያል። ብትበደሉ አይሻልምን? ብትታለሉስ አይሻልምን?

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 እንግዲህ ፈጽሞ የእርስ በእርስ ሙግት በመካከላችሁ መፍጠር ለእናንተ ሽንፈት ነው። ይልቅስ ብትበደሉ አይሻልምን? እንዲሁም ብትታለሉ አይሻልምን?

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 እንዲያውም እርስ በርሳችሁ ተካሳችሁ መሟገት ራሱ ለእናንተ ውርደት ነው፤ ይልቅስ እናንተ ብትበደሉ አይሻልምን? እንዲሁም እናንተ ብትታለሉ አይሻልምን?

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 እንግዲህ ፈጽሞ የእርስ በርስ ሙግት እንዳለባችሁ በእናንተ ጉድለት ነው። ብትበደሉ አይሻልምን? ብትታለሉስ አይሻልምን?

Ver Capítulo Cópia de




1 ቆሮንቶስ 6:7
12 Referências Cruzadas  

የዚያን ጊዜ እግዚአብሔርን መፍራት ታውቃለህ፥ አምላክን ማወቅንም ታገኛለህ።


ጠላቴን እበቀለዋለሁ አትበል፤ ነገር ግን እንዲረዳህ እግዚአብሔርን ተማመን።


ልባ​ቸው ተከ​ፈለ፤ አሁ​ንም ይጠ​ፋሉ፤ እርሱ መሠ​ዊ​ያ​ቸ​ውን ያፈ​ር​ሳል፤ ሐው​ል​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም ያጠ​ፋል።


ዘኬ​ዎ​ስም ቆመና ጌታ​ች​ንን እን​ዲህ አለው፥ “ጌታዬ ሆይ፥ አሁን የገ​ን​ዘ​ቤን እኩ​ሌታ ለነ​ዳ​ያን እሰ​ጣ​ለሁ፤ የበ​ደ​ል​ሁ​ትም ቢኖር ስለ አንድ ፋንታ አራት እጥፍ እከ​ፍ​ለ​ዋ​ለሁ።”


ጕን​ጭ​ህን ለሚ​መ​ታ​ህም ሁለ​ተ​ኛ​ይ​ቱን ስጠው፤ መጐ​ና​ጸ​ፊ​ያ​ህን ለሚ​ወ​ስ​ድም ቀሚ​ስ​ህን ደግሞ አት​ከ​ል​ክ​ለው።


ማንም ለሌላው በክፉ ፈንታ ክፉ እንዳይመልስ ተጠንቀቁ፤ ነገር ግን ሁልጊዜ እርስ በርሳችሁ ለሁሉም መልካሙን ለማድረግ ትጉ።


ክፉን በክፉ ፈንታ ወይም ስድብን በስድብ ፈንታ አትመልሱ፤ በዚህ ፈንታ ባርኩ እንጂ፤ በረከትን ልትወርሱ ለዚህ ተጠርታችኋልና።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios