Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




1 ቆሮንቶስ 6:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 ከአ​መ​ን​ዝራ ጋር የተ​ገ​ናኘ ከእ​ር​ስዋ ጋር አንድ አካል እን​ዲ​ሆን አታ​ው​ቁ​ምን? መጽ​ሐፍ፥ “ሁለቱ አንድ አካል ይሆ​ናሉ” ብሎ​አ​ልና።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 ወይስ ከዝሙት ዐዳሪ ጋራ የሚተባበር ሰው ከርሷ ጋራ አንድ ሥጋ እንደሚሆን አታውቁምን? “ሁለቱም አንድ ሥጋ ይሆናሉ” ተብሏልና።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 ወይስ ከአመንዝራ ጋር የሚገናኝ አንድ አካል እንዲሆን አታውቁምን? “ሁለቱ አንድ ሥጋ ይሆናሉ፤” ተብሏልና።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 ከአመንዝራ ሴት ጋር የሚገናኝ ሰው ከእርስዋ ጋር አንድ አካል መሆኑን ታውቁ የለምን? “ሁለቱም አንድ አካል ይሆናሉ” ተብሎ ተጽፎአልና።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 ወይስ ከጋለሞታ ጋር የሚተባበር አንድ ሥጋ እንዲሆን አታውቁምን? ሁለቱ አንድ ሥጋ ይሆናሉ ተብሎአልና።

Ver Capítulo Cópia de




1 ቆሮንቶስ 6:16
11 Referências Cruzadas  

ስለ​ዚህ ሰው አባ​ቱ​ንና እና​ቱን ይተ​ዋል፤ ሚስ​ቱ​ንም ይከ​ተ​ላል ፤ ሁለ​ቱም አንድ ሥጋ ይሆ​ናሉ።


እነ​ር​ሱም፥ “እኅ​ታ​ች​ንን እንደ አመ​ን​ዝራ አድ​ር​ገው ለምን አዋ​ረ​ዷት?” አሉት።


ይሁ​ዳም በአ​ያት ጊዜ ዘማ መሰ​ለ​ችው፤ ፊቷን ተሸ​ፍና ነበ​ርና አላ​ወ​ቃ​ትም።


እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ከሦ​ስት ወር በኋላ ለይ​ሁዳ፥ “ምራ​ትህ ትዕ​ማር ሴሰ​ነች፤ እነሆ፥ በዝ​ሙት ፀነ​ሰች” ብለው ነገ​ሩት። ይሁ​ዳም፥ “አው​ጡ​አ​ትና በእ​ሳት ትቃ​ጠል” አለ።


ሁለቱም አንድ ሥጋ ይሆናሉ፤ ስለዚህ አንድ ሥጋ ናቸው እንጂ ወደ ፊት ሁለት አይደሉም።


የዚ​ህ​ንስ ዓለም ዳኝ​ነት ተዉ​ትና በመ​ላ​እ​ክት ስንኳ እን​ድ​ን​ፈ​ርድ አታ​ው​ቁ​ምን?


“ስለ​ዚ​ህም ወንድ አባ​ቱ​ንና እና​ቱን ይተ​ዋል፤ ከሚ​ስ​ቱም ጋር አንድ ይሆ​ናል፤ ሁለ​ቱም አንድ አካል ይሆ​ናሉ።”


ዘማ ረአ​ብም በእ​ም​ነት ከከ​ሓ​ዲ​ዎች ጋር አል​ጠ​ፋ​ችም፤ ጕበ​ኞ​ችን በሰ​ላም ተቀ​ብላ ሰው​ራ​ቸ​ዋ​ለ​ችና።


ሶም​ሶ​ንም ወደ ጋዛ ሄደ፥ በዚ​ያም ጋለ​ሞታ ሴት አይቶ ወደ እር​ስዋ ገባ።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios