Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




1 ዜና መዋዕል 6:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 የእ​ን​በ​ረ​ምም ልጆች፤ አሮን፥ ሙሴ፥ ማር​ያም። የአ​ሮ​ንም ልጆች፤ ናዳብ፥ አብ​ዩድ፥ አል​ዓ​ዛር፥ ኢታ​ምር።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 የእንበረም ልጆች፤ አሮን፣ ሙሴ፣ ማርያም። የአሮን ወንዶች ልጆች፤ ናዳብ፣ አብዩድ፣ አልዓዛር፣ ኢታምር።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 የእንበረምም ልጆች፤ አሮን፥ ሙሴ፥ ማርያም ነበሩ። የአሮን ልጆች፤ ናዳብ፥ አብዩድ፥ አልዓዛር፥ ኢታምር ነበሩ።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 ዓምራምም አሮንና ሙሴ ተብለው የሚጠሩ ሁለት ወንዶች ልጆችና ማርያም ተብላ የምትጠራ አንዲት ሴት ልጅ ወለደ። አሮንም ናዳብ፥ አቢሁ፥ አልዓዛርና ኢታማር ተብለው የሚጠሩ ወንዶች ልጆች ነበሩት።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 የእንበረምም ልጆች፤ አሮን፥ ሙሴ፥ ማርያም። የአሮን ልጆች፤ ናዳብ፥ አቢሁ፥ አልዓዛር፥ ኢታምር።

Ver Capítulo Cópia de




1 ዜና መዋዕል 6:3
18 Referências Cruzadas  

ከዑ​ዝ​ኤል ልጆች፤ አለ​ቃው አሚ​ና​ዳብ፥ ወን​ድ​ሞ​ቹም መቶ ዐሥራ ሁለት።


የቀ​ዓት ልጆች እን​በ​ረም፥ ይስ​ዓር፦ ኬብ​ሮን፥ ዑዝ​ኤል አራት ነበሩ።


የእ​ን​በ​ረም ልጆች አሮ​ንና ሙሴ ነበሩ፤ አሮ​ንም ለቅ​ድ​ስተ ቅዱ​ሳን የተ​ቀ​ደሰ ይሆን ዘንድ ተመ​ረጠ፤ እር​ሱና ልጆቹ ለዘ​ለ​ዓ​ለም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ያጥ​ኑና ያገ​ለ​ግሉ ነበር፤ በስ​ሙም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይባ​ርኩ ነበር።


ከኢ​ስ​ዓ​ራ​ው​ያን ሰሎ​ሞት፤ ከሰ​ሎ​ሞት ልጆች ኤናት፤


የቀ​ዓ​ትም ልጆች፤ እን​በ​ረም፥ ይስ​ዓር፥ ኬብ​ሮን፥ ዑዝ​ኤል።


አል​ዓ​ዛር ፊን​ሐ​ስን ወለደ፤ ፊን​ሐ​ስም አቢ​ሱን ወለደ፤


የአ​ሮን እኅት ነቢ​ይቱ ማር​ያ​ምም ከበሮ በእ​ጅዋ ወሰ​ደች፤ ሴቶ​ችም ሁሉ በከ​በ​ሮና በዝ​ማሬ በኋ​ላዋ ወጡ።


እኅ​ቱም ምን እን​ደ​ሚ​ደ​ር​ስ​በት ታውቅ ዘንድ በሩቅ ቆማ ትጐ​በ​ኘው ነበር።


የዚ​ያም ሕፃን እኅት ለፈ​ር​ዖን ልጅ፥ “ሕፃ​ኑን ታጠ​ባ​ልሽ ዘንድ ሄጄ የም​ታ​ጠባ ሴት ከዕ​ብ​ራ​ው​ያን ሴቶች ልጥ​ራ​ል​ሽን?” አለ​ቻት።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን አለው፥ “አንተ፥ አሮ​ንም፥ ናዳ​ብም፥ አብ​ዩ​ድም፥ ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሰባ ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ውጡ፤ በሩ​ቁም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስገዱ፤


“አን​ተም ወን​ድ​ም​ህን አሮ​ንን ከእ​ር​ሱም ጋር ልጆ​ቹን ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች መካ​ከል ለይ​ተህ በክ​ህ​ነት ያገ​ለ​ግ​ሉኝ ዘንድ ወደ አንተ አቅ​ርብ፤ አሮ​ንን የአ​ሮ​ን​ንም ልጆች፥ ናዳ​ብን፥ አብ​ዩ​ድ​ንም፥ አል​ዓ​ዛ​ር​ንም ኢታ​ም​ር​ንም አቅ​ርብ።


እን​በ​ረ​ምም የአ​ባ​ቱን ወን​ድም ልጅ ዮካ​ብ​ድን አገባ፤ አሮ​ን​ንና ሙሴን፥ እኅ​ታ​ቸ​ው​ንም ማር​ያ​ምን ወለ​ደ​ች​ለት፤ የእ​ን​በ​ረ​ምም የሕ​ይ​ወቱ ዘመን መቶ ሠላሳ ሰባት ዓመት ነው።


አሮ​ንም የአ​ሚ​ና​ዳ​ብን ልጅ የነ​አ​ሶ​ንን እኅት ኤል​ሳ​ቤ​ጥን አገባ። እር​ስ​ዋም ናዳ​ብ​ንና አብ​ዩ​ድን፥ አል​ዓ​ዛ​ር​ንና ኢታ​ም​ርን ወለ​ደ​ች​ለት።


የአ​ሮ​ንም ልጆች ናዳ​ብና አብ​ዩድ በየ​ራ​ሳ​ቸው ጥና​ውን ወስ​ደው እሳት አደ​ረ​ጉ​በት፤ በላ​ዩም ዕጣን ጨመ​ሩ​በት፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያላ​ዘ​ዛ​ቸ​ውን ሌላ እሳት አቀ​ረቡ።


ሙሴም አሮ​ንን፥ የተ​ረ​ፉ​ለ​ትን ልጆ​ቹን አል​ዓ​ዛ​ር​ንና ኢታ​ም​ርን አላ​ቸው፥ “ቅዱሰ ቅዱ​ሳን ነውና ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከሆ​ነው ከእ​ሳት ቍር​ባን የቀ​ረ​ውን የስ​ን​ዴ​ውን ቍር​ባን ውሰዱ፤ ቂጣም አድ​ር​ጋ​ችሁ በመ​ሠ​ዊ​ያው አጠ​ገብ ብሉት፤


ሙሴም የኀ​ጢ​አ​ቱን መሥ​ዋ​ዕት ፍየል እጅግ ፈለ​ገው፤ በፈ​ለ​ገ​ውም ጊዜ እነሆ ተቃ​ጥሎ ነበር፤ ሙሴም የቀ​ሩ​ትን የአ​ሮ​ንን ልጆች አል​ዓ​ዛ​ር​ንና ኢታ​ም​ርን ተቈ​ጣ​ቸው፤ እን​ዲ​ህም አላ​ቸው፦


ከግብጽ ምድር አውጥቼሃለሁ፥ ከባርነት ቤትም ተቤዥቼሃለሁ፥ በፊትህም ሙሴንና አሮንን ማርያምንም ልኬልህ ነበር።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios