Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




1 ዜና መዋዕል 5:25 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

25 የአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም አም​ላክ በደሉ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከፊ​ታ​ቸው ባጠ​ፋ​ቸው በም​ድሩ አሕ​ዛብ አማ​ል​ክት አመ​ነ​ዘሩ።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

25 ይሁን እንጂ ለአባቶቻቸው አምላክ አልታመኑም፤ እግዚአብሔር ከፊታቸው ያጠፋቸውን የምድሪቱን አሕዛብ አማልክት በማምለክ አመነዘሩ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

25 የአባቶቻቸውንም አምላክ በደሉ፥ እግዚአብሔርም ከፊታቸው ባጠፋቸው በምድሩ አሕዛብ አማልክት አመነዘሩ።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

25 ሕዝቡ ለቀድሞ አባቶቹ አምላክ ታማኝ ሆኖ አልተገኘም፤ እንዲያውም እግዚአብሔርን ትቶ ከምድሪቱ ላይ ላስወገደለት ሕዝብ አማልክት ሰገደ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

25 የአባቶቻቸውንም አምላክ በደሉ፤ እግዚአብሔርም ከፊታቸው ባጠፋቸው በምድሩ አሕዛብ አማልክት አመነዘሩ።

Ver Capítulo Cópia de




1 ዜና መዋዕል 5:25
14 Referências Cruzadas  

በዘ​መ​ኑም የአ​ሶር ንጉሥ ፎሐ በም​ድ​ሪቱ ላይ ወጣ፤ ምና​ሔ​ምም የፎሐ እጅ ከእ​ርሱ ጋር እን​ዲ​ሆን አንድ ሺህ መክ​ሊት ብር ሰጠው።


የአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ቤቶች አለ​ቆች እነ​ዚህ ነበሩ፤ ዔፌር፥ ይስዔ፥ ኤሊ​ኤል፥ ዓዝ​ር​ኤል፥ ኢይ​ር​ምያ፥ ሆዳ​ይዋ፥ ኢየ​ድ​ኤል፤ እነ​ርሱ ጽኑ​ዓን ኀያ​ላን የታ​ወቁ ሰዎች የአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ቤቶች አለ​ቆች ነበሩ።


እስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ ስለ ኀጢ​አ​ታ​ቸው ወደ ባቢ​ሎን ከተ​ማ​ረኩ በኋላ፥ በየ​ት​ው​ል​ዳ​ቸው ተቈ​ጠሩ፤ እነ​ሆም በእ​ስ​ራ​ኤ​ልና በይ​ሁዳ ነገ​ሥ​ታት መጽ​ሐፍ ተጽ​ፈ​ዋል።


በዚ​ያች ምድር ከሚ​ኖሩ ሰዎች ጋር ቃል ኪዳን እን​ዳ​ታ​ደ​ርግ፥ እነ​ርሱ አም​ላ​ኮ​ቻ​ቸ​ውን ተከ​ት​ለው በአ​መ​ነ​ዘ​ሩና በሠ​ዉ​ላ​ቸው ጊዜ እን​ዳ​ይ​ጠ​ሩህ፥ ከመ​ሥ​ዋ​ዕ​ታ​ቸ​ውም እን​ዳ​ት​በላ፥


ወደ ሆሴዕ የመጣ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የቃሉ መጀ​መ​ሪያ ይህ ነው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሆሴ​ዕን፥ “ምድ​ሪቱ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ርቃ ታመ​ነ​ዝ​ራ​ለ​ችና ሂድ፤ ዘማ​ዊ​ቱን ሴትና የዘ​ማ​ዊ​ቱን ልጆች ለአ​ንተ ውሰድ” አለው።


እስ​ራ​ኤል ሆይ! ከአ​ም​ላ​ክህ ርቀህ አመ​ን​ዝ​ረ​ሃ​ልና እንደ አሕ​ዛብ ደስ አይ​በ​ልህ፤ ሐሴ​ት​ንም አታ​ድ​ርግ፤ ከእ​ህ​ሉና ከወ​ይኑ አው​ድማ ሁሉ ይልቅ የግ​ል​ሙ​ትና ዋጋን ወድ​ደ​ሃል።


በግምባርዋም ምስጢር የሆነ ስም “ታላቂቱ ባቢሎን፥ የጋለሞታዎችና የምድር ርኵሰት እናት” ተብሎ ተጻፈ።


ከግ​ብፅ ምድ​ርም ያወ​ጣ​ቸ​ውን የአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ተዉ፤ ሌሎ​ች​ንም በዙ​ሪ​ያ​ቸው ያሉ የአ​ሕ​ዛ​ብን አማ​ል​ክት ተከ​ተሉ፤ ሰገ​ዱ​ላ​ቸ​ውም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም አስ​ቈ​ጡት።


ሌሎች አማ​ል​ክ​ትን ተከ​ት​ለው አመ​ነ​ዘሩ፤ ሰገ​ዱ​ላ​ቸ​ውም እንጂ፥ መሳ​ፍ​ን​ቶ​ቻ​ቸ​ውን አል​ሰ​ሙም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም አስ​ቈ​ጡት፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ቃል እን​ዳ​ይ​ሰሙ አባ​ቶ​ቻ​ቸው ይሄ​ዱ​ባት የነ​በ​ረ​ች​ውን መን​ገድ ፈጥ​ነው ተዉ​አት፤ እን​ዲ​ሁም አላ​ደ​ረ​ጉም።


እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ጌዴ​ዎን ከሞተ በኋላ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ተመ​ለሱ፤ በዓ​ሊ​ም​ንም ተከ​ት​ለው አመ​ነ​ዘሩ፤ በዓ​ሊ​ምም አም​ላክ ይሆ​ና​ቸው ዘንድ ከእ​ርሱ ጋር ቃል ኪዳን ገቡ።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios