Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




1 ዜና መዋዕል 5:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 ሰልፉ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ነበ​ረና ብዙ ሰዎች ተገ​ድ​ለው ወደቁ፤ እስከ ምር​ኮም ዘመን ድረስ በስ​ፍ​ራ​ቸው ተቀ​መጡ።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 ውጊያው የእግዚአብሔር ስለ ነበር፣ ሌሎችም ብዙ ሰዎች ተገደሉ። እስከ ምርኮ ጊዜ ድረስ ምድሪቱ በእጃቸው ነበረች።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 ሰልፉ ከእግዚአብሔር ዘንድ ነበረና ብዙ ሰዎች ተገድለው ወደቁ፤ እስከ ምርኮም ዘመን ድረስ በስፍራቸው ተቀመጡ።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 ጦርነቱ እግዚአብሔር የፈቀደው ስለ ነበረ፥ ከጠላት ወገን ብዙ ሰዎችን ገደሉ፤ እነርሱም ራሳቸው ተማርከው እስከ ተወሰዱበት ጊዜ ድረስ በምድሪቱ ላይ መኖራቸውን ቀጠሉ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 ሰልፉ ከእግዚአብሔር ዘንድ ነበረና ብዙ ሰዎች ተገድለው ወደቁ፤ እስከ ምርኮም ዘመን ድረስ በስፍራቸው ተቀመጡ።

Ver Capítulo Cópia de




1 ዜና መዋዕል 5:22
11 Referências Cruzadas  

“ጋድን ሽፍ​ቶች ቀሙት፤ እር​ሱም ፍለ​ጋ​ቸ​ውን ተከ​ታ​ትሎ ቀማ​ቸው።


በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ በፋ​ቁሔ ዘመን የአ​ሶር ንጉሥ ቴል​ጌ​ል​ቴ​ል​ፌ​ል​ሶር መጣ፤ ኢዮ​ንና አቤ​ል​ቤ​ት​መ​ዓ​ካን፥ ያኖ​ዋ​ንም፥ ቃዴ​ስ​ንና አሶ​ር​ንም፥ ገለ​ዓ​ድ​ንና ገሊ​ላ​ንም፥ የን​ፍ​ታ​ሌ​ም​ንም ሀገር ሁሉ ወሰደ፤ ወደ አሶ​ርም አፈ​ለ​ሳ​ቸው።


በሆ​ሴ​ዕም በዘ​ጠ​ነ​ኛው ዓመት የአ​ሦር ንጉሥ ሰማ​ር​ያን ያዘ፤ እስ​ራ​ኤ​ል​ንም ወደ አሶር አፈ​ለሰ፤ በአ​ላ​ሔና በአ​ቦር፤ በጎ​ዛ​ንም ወንዝ፤ በሜ​ዶ​ንም ከተ​ሞች አኖ​ራ​ቸው።


በስ​ማ​ቸው የተ​ጻፉ እነ​ዚ​ህም በይ​ሁዳ ንጉሥ በሕ​ዝ​ቅ​ያስ ዘመን መጥ​ተው ድን​ኳ​ኖ​ቻ​ቸ​ው​ንና በዚያ የተ​ገ​ኙ​ትን ምዑ​ና​ው​ያ​ንን መቱ፥ እስከ ዛሬም ድረስ ፈጽ​መው አጠ​ፉ​አ​ቸው፤ በዚ​ያም ለመ​ን​ጎ​ቻ​ቸው መሰ​ማ​ሪያ ነበ​ርና በስ​ፍ​ራ​ቸው ተቀ​መጡ።


ከከ​ብ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም አምሳ ሺህ ግመ​ሎች፥ ሁለት መቶ አምሳ ሺህም በጎች፥ ሁለት ሺህም አህ​ዮች፥ ከሰ​ዎ​ችም መቶ ሺህ ማረኩ።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም አም​ላክ የአ​ሦ​ርን ንጉሥ የፋ​ሎ​ክን መን​ፈስ፥ የአ​ሦ​ር​ንም ንጉሥ የቴ​ል​ጌ​ል​ቴ​ል​ፌ​ል​ሶ​ርን መን​ፈስ አስ​ነሣ፤ የሮ​ቤ​ል​ንና የጋ​ድን ልጆች የም​ና​ሴ​ንም ነገድ እኩ​ሌታ አፈ​ለሰ፥ እስከ ዛሬም ወዳ​ሉ​በት ወደ አላ​ሔና ወደ ኦቦር፥ ወደ ሃራ​ንና ወደ ጎዛን ወንዝ አመ​ጣ​ቸው።


ልጁ ሕል​ቃና፤ ልጁ ሱፌ፤ ልጁ ናሔት፤


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንና በዓ​ለት ላይ በሚ​ኖሩ ዓረ​ባ​ው​ያን፥ በም​ዕ​ዑ​ና​ው​ያ​ንም ላይ አጸ​ናው።


ከእ​ርሱ ጋር የሥጋ ክንድ ነው፤ ከእኛ ጋር ያለው ግን የሚ​ረ​ዳን የሚ​ዋ​ጋ​ል​ንም አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው።” ሕዝ​ቡም በይ​ሁዳ ንጉሥ በሕ​ዝ​ቅ​ያስ ቃል ተጽ​ናና።


እን​ግ​ዲህ ስለ​ዚህ ምን እን​ላ​ለን? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእና ጋር ከሆነ ማን ይች​ለ​ናል?


አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ነገ​ረን ስለ እና​ንተ የሚ​ዋጋ እርሱ ነውና ከእ​ና​ንተ አንዱ ሰው ሺህ ሰውን ያሳ​ድ​ዳል።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios