Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




1 ዜና መዋዕል 17:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 ንጉ​ሡም ዳዊት ገባ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ተቀ​ምጦ እን​ዲህ አለ፥ “አቤቱ አም​ላክ ሆይ፥ ለዘ​ለ​ዓም የወ​ደ​ድ​ኸኝ እኔ ማን ነኝ? ቤቴስ ምን​ድን ነው?

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 ከዚያም ንጉሥ ዳዊት ገባ፤ በእግዚአብሔር ፊት ተቀምጦም እንዲህ አለ፤ “እግዚአብሔር አምላክ ሆይ፤ ለመሆኑ እስከዚህ ያደረስኸኝ እኔ ማን ነኝ? ቤቴስ ምንድን ነው?

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 ንጉሡም ዳዊት ገባ፥ በጌታም ፊት ተቀምጦ እንዲህ አለ፦ “አቤቱ አምላክ ሆይ! እስከዚህ ያደረስኸኝ እኔ ማን ነኝ? ቤቴስ ምንድነው?

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 ከዚህ በኋላ ንጉሥ ዳዊት እግዚአብሔር ወደሚመለክበት ድንኳን ሄደ፤ ተቀምጦም እንዲህ ሲል ጸለየ፤ “እግዚአብሔር አምላክ ሆይ፥ እኔ ይህን ሁሉ ነገር ታደርግልኝ ዘንድ እኔ ማነኝ? ቤተሰቤስ ምንድን ነው?

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 ንጉሡም ዳዊት ገባ፤ በእግዚአብሔርም ፊት ተቀምጦ እንዲህ አለ “አቤቱ አምላክ ሆይ! እስከዚህ ያደረስኸኝ እኔ ማን ነኝ? ቤቴስ ምንድር ነው?

Ver Capítulo Cópia de




1 ዜና መዋዕል 17:16
15 Referências Cruzadas  

ለባ​ሪ​ያህ በአ​ደ​ረ​ግ​ኸው በም​ሕ​ረ​ት​ህና በእ​ው​ነ​ት​ህም ሁሉ በጎ​ውን አድ​ር​ግ​ልኝ፤ በት​ሬን ብቻ ይዤ ይህን ዮር​ዳ​ኖ​ስን ተሻ​ግሬ ነበ​ርና፥ አሁን ግን የሁ​ለት ክፍል ሠራ​ዊት ሆንሁ።


ንጉሡ ዳዊ​ትም ገባ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ተቀ​ምጦ እን​ዲህ አለ፥ “ጌታዬ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሆይ፥ ይህን ያህል የወ​ደ​ድ​ኸኝ እኔ ማን ነኝ? ቤቴስ ምን​ድን ነው?


ሕዝ​ቅ​ያ​ስም ደብ​ዳ​ቤ​ውን ከመ​ል​እ​ክ​ተ​ኞች እጅ ተቀ​ብሎ አነ​በ​በው፤ ሕዝ​ቅ​ያ​ስም ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ወጥቶ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ዘረ​ጋው።


እን​ደ​ዚህ ነገር ሁሉ እን​ደ​ዚ​ህም ራእይ ሁሉ ነቢዩ ናታን ለዳ​ዊት ነገ​ረው።


አም​ላክ ሆይ፥ ይህ በፊ​ትህ ጥቂት ነበረ፤ ስለ አገ​ል​ጋ​ይህ ቤት ደግሞ ለሩቅ ዘመን ተና​ገ​ርህ፤ እንደ አንድ ባለ ማዕ​ረግ ሰው ተመ​ለ​ከ​ት​ኸኝ። አቤቱ፥ አም​ላክ ሆይ፥ ከፍ ከፍ አደ​ረ​ግ​ኸኝ።


ሁሉ ከአ​ንተ ዘንድ ነውና፥ ከእ​ጅ​ህም የተ​ቀ​በ​ል​ነ​ውን ሰጥ​ተ​ን​ሃ​ልና ይህን ያህል ችለን ልና​ቀ​ር​ብ​ልህ እኔ ማን ነኝ? ሕዝ​ቤስ ማን ነው?


ሰሎ​ሞ​ንም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አለው፥ “ከአ​ባቴ ከዳ​ዊት ጋር ታላቅ ምሕ​ረ​ትን አድ​ር​ገ​ሃል፤ በእ​ር​ሱም ፋንታ አን​ግ​ሠ​ኸ​ኛል።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታላቅ ነው፥ ምስ​ጋ​ና​ውም እጅግ ብዙ ነው፤ ለታ​ላ​ቅ​ነ​ቱም ዳርቻ የለ​ውም።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አዳ​ነ​ኝና ለታ​ላ​ቁም፥ ለታ​ና​ሹም እየ​መ​ሰ​ከ​ርሁ እስከ ዛሬ ደረ​ስሁ፤ ይደ​ረግ ዘንድ ካለው፥ ነቢ​ያት ከተ​ና​ገ​ሩት፥ ሙሴም ከተ​ና​ገ​ረው ሌላ ያስ​ተ​ማ​ር​ሁት የለም።


እር​ሱም እን​ዲህ ካለ ሞት አዳ​ነን፤ ያድ​ነ​ን​ማል፤ አሁ​ንም እን​ደ​ሚ​ያ​ድ​ነን እር​ሱን እን​ታ​መ​ና​ለን።


ከቅ​ዱ​ሳን ሁሉ ለማ​ንስ ለእኔ የማ​ይ​መ​ረ​መ​ረ​ውን የክ​ር​ስ​ቶ​ስን ባለ​ጸ​ግ​ነት ለአ​ሕ​ዛብ አስ​ተ​ምር ዘንድ ይህን ጸጋ ሰጠኝ።


እር​ሱም፥ “ጌታ ሆይ! እሺ፥ እስ​ራ​ኤ​ልን በምን አድ​ና​ለሁ? ወገኔ በም​ናሴ ነገድ ዘንድ ጥቂ​ቶች ናቸው፤ እኔም በአ​ባቴ ቤት የሁሉ ታናሽ ነኝ” አለው።


ሳሙ​ኤ​ልም አንድ ድን​ጋይ ወስዶ በመ​ሴ​ፋና በአ​ሮ​ጌው ከተማ መካ​ከል አኖ​ረው፤ ስሙ​ንም፥ “እስከ አሁን ድረስ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ረድ​ቶ​ናል” ሲል “አቤ​ን​ኤ​ዜር” ብሎ ጠራው። እብነ ረድ​ኤት ማለት ነው።


ሳኦ​ልም መልሶ፥ “እኔ ከእ​ስ​ራ​ኤል ነገ​ዶች ከሚ​ያ​ንስ ወገን የሆ​ንሁ ብን​ያ​ማዊ ሰው አይ​ደ​ለ​ሁ​ምን? ወገ​ኔስ ከብ​ን​ያም ነገድ ወገ​ኖች ሁሉ የሚ​ያ​ንስ አይ​ደ​ለ​ምን? እን​ዲ​ህስ ያለ​ውን ነገር ለምን ነገ​ር​ኸኝ?” አለ።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios