Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




1 ዜና መዋዕል 15:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 በቀ​ድሞ ሥራ​ችን አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እርስ በር​ሳ​ችን አላ​ጠ​ፋ​ንም፤ በጦ​ር አል​ፈ​ለ​ገ​ን​ምና” አላ​ቸው።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 የአምላካችን የእግዚአብሔር ቍጣ በላያችን ላይ እንዲህ የነደደው እናንተ ሌዋውያኑ ቀድሞም ስላላመጣችሁት ነው፤ እኛም ብንሆን ምን ማድረግ እንዳለብን በታዘዘው መሠረት አልጠየቅነውም።”

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 ቀድሞም አልተሸከማችሁትምና፥ እንደ ሥርዓቱም አልፈለግነውምና ጌታ አምላካችን በመካከላችን ቊጣውን አወረደ።”

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 ከዚህ በፊት እናንተ ተገኝታችሁ ታቦቱን ባለመሸከማችሁ በተደነገገው ሥርዓት መሠረት ስላላገለገልነው አምላካችን እግዚአብሔር ቀጥቶናል።”

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 ቀድሞም አልተሸከማችሁምና፥ እንደ ሥርዐቱም አልፈለግነውምና አምላካችን እግዚአብሔር በመካከላችን ስብራት አደረገ፤” አላቸው።

Ver Capítulo Cópia de




1 ዜና መዋዕል 15:13
13 Referências Cruzadas  

የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ታቦት በአ​ዲስ ሰረ​ገላ ላይ ጫኑ​አት፥ በኮ​ረ​ብ​ታ​ውም ላይ ከነ​በ​ረው ከአ​ሚ​ና​ዳብ ቤት አመ​ጡ​አት፤ የአ​ሚ​ና​ዳብ ልጆ​ችም ዖዛና ወን​ድ​ሞቹ ታቦቷ ያለ​ች​በ​ትን ሰረ​ገላ ይነዱ ነበር።


ከሳ​ኦ​ልም ዘመን ጀምሮ አል​ፈ​ለ​ጓ​ት​ምና የአ​ም​ላ​ካ​ችን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታቦት ወደ እኛ እን​መ​ል​ሳት” አላ​ቸው።


በዚ​ያን ጊዜም ዳዊት፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታቦት ይሸ​ከሙ ዘንድ፥ ለዘ​ለ​ዓ​ለ​ሙም ያገ​ለ​ግ​ሉት ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከመ​ረ​ጣ​ቸው ከሌ​ዋ​ው​ያን በቀር ማንም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታቦት ይሸ​ከም ዘንድ አይ​ገ​ባ​ውም” አለ።


አሮ​ንና ልጆቹ መቅ​ደ​ሱ​ንና የመ​ቅ​ደ​ሱን ዕቃ ሁሉ ሸፍ​ነው ከጨ​ረሱ በኋላ ሰፈሩ ሲነሣ የቀ​ዓት ልጆች ሊሸ​ከ​ሙት ይገ​ባሉ። እን​ዳ​ይ​ሞቱ ግን ንዋየ ቅድ​ሳ​ቱን አይ​ንኩ። በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ዘንድ የቀ​ዓት ልጆች ሸክም ይህ ነው።


ለቀ​ዓት ልጆች ግን መቅ​ደ​ሱን ማገ​ል​ገል የእ​ነ​ርሱ ነውና፥ በት​ከ​ሻ​ቸ​ውም ይሸ​ከ​ሙት ነበ​ርና ምንም አል​ሰ​ጣ​ቸ​ውም።


ወን​ድ​ሞች ሆይ፥ አመ​ሰ​ግ​ና​ች​ኋ​ለሁ፤ ዘወ​ትር ታስ​ቡ​ኛ​ላ​ች​ሁና፤ ያስ​ተ​ማ​ር​ኋ​ች​ሁ​ንም ትም​ህ​ርት ጠብ​ቃ​ች​ኋ​ልና።


ነገር ግን ሁሉን በአ​ገ​ባ​ብና በሥ​ር​ዐት አድ​ርጉ፤


ሙሴም ይህ​ችን ሕግ ጻፈ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም የቃል ኪዳ​ኑን ታቦት ይሸ​ከሙ ለነ​በ​ሩት ለሌዊ ልጆች ለካ​ህ​ናቱ፥ ለእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ሁሉ ሰጣት።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios