Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




1 ዜና መዋዕል 13:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 በዚ​ያም ቀን ዳዊት፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታቦት ወደ እኔ እን​ዴት አመ​ጣ​ለሁ?” ብሎ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፈራ።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 ዳዊት በዚያ ዕለት እግዚአብሔርን ስለ ፈራ፣ “ታዲያ የእግዚአብሔርን ታቦት ወደ እኔ እንዴት ማምጣት እችላለሁ?” አለ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 በዚያም ቀን ዳዊት፦ “የእግዚአብሔርን ታቦት ወደ እኔ እንዴት አመጣለሁ?” ብሎ እግዚአብሔርን ፈራ።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 ከዚህ በኋላ ዳዊት እግዚአብሔርን እጅግ ስለ ፈራ “እንግዲህ ይህን የቃል ኪዳን ታቦት ወደ ቤቴ እንዴት መውሰድ እችላለሁ?” አለ፤

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 በዚያም ቀን ዳዊት “የእግዚአብሔርን ታቦት ወደ እኔ እንዴት አመጣለሁ?” ብሎ እግዚአብሔርን ፈራ።

Ver Capítulo Cópia de




1 ዜና መዋዕል 13:12
12 Referências Cruzadas  

“በውኑ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከሰው ጋር በም​ድር ላይ ይኖ​ራ​ልን? እነሆ ሰማይ ከሰ​ማ​ያ​ትም በላይ ያለው ሰማይ ይይ​ዝህ ዘንድ አይ​ች​ልም፤ ይል​ቁ​ንስ እኔ ለስ​ምህ የሠ​ራ​ሁት ቤት እን​ዴት ያንስ!


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ዖዛን ስለ ሰበ​ረው ዳዊት አዘነ፤ እስከ ዛሬም ድረስ የዚ​ያን ስፍራ ስም “የዖዛ ስብ​ራት” ብሎ ጠራው።


ዳዊ​ትም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታቦት ወደ ጌት ሰው ወደ አቢ​ዳራ ቤት አሳ​ለ​ፋት እንጂ ወደ እርሱ ወደ ዳዊት ከተማ አላ​መ​ጣ​ትም።


ዳዊት ግን ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​አክ ሰይፍ የተ​ነሣ ስለ ፈራ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ለመ​ጠ​የቅ ወደ​ዚያ ይሄድ ዘንድ አል​ቻ​ለም።


እኔም፥ “ከን​ፈ​ሮች የረ​ከ​ሱ​ብኝ ሰው በመ​ሆኔ፥ ከን​ፈ​ሮ​ቻ​ቸው በረ​ከ​ሱ​ባ​ቸው ሕዝብ መካ​ከል በመ​ቀ​መጤ ዐይ​ኖች የሠ​ራ​ዊ​ትን ጌታ ንጉ​ሡን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ስለ አዩ ጠፍ​ቻ​ለ​ሁና ወዮ​ልኝ!” አልሁ።


አንድ መክሊትም የተቀበለው ደግሞ ቀርቦ ‘ጌታ ሆይ! ካልዘራህባት የምታጭድ ካልበተንህባትም የምትሰበስብ ጨካኝ ሰው መሆንህን አውቃለሁ፤


የቤ​ት​ሳ​ሚ​ስም ሰዎች፥ “በዚህ በቅ​ዱሱ አም​ላክ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ማለፍ ማን ይች​ላል? የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታቦት ከእኛ ወጥታ ወደ ማን ትሄ​ዳ​ለች?” አሉ።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios