Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




መዝሙር 76:5 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 ልበ ሙሉ የሆኑት ተዘርፈዋል፤ አንቀላፍተውም ተኝተዋል፤ ከኀያላኑም መካከል፣ እጁን ማንቀሳቀስ የቻለ የለም።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 አንተ በዘለዓለም ተራሮች ሆነህ በድንቅ ታበራለህ።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 ጀግኖች ወታደሮች የማረኩትን ተቀሙ፤ እጃቸውንም ማንሣት አቅቶአቸው የመጨረሻ እንቅልፍ አንቀላፉ

Ver Capítulo Cópia de

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 የድ​ሮ​ውን ዘመን ዐሰ​ብሁ፤ የዘ​ለ​ዓ​ለ​ሙን ዓመ​ታት ዐሰ​ብሁ፤ አነ​በ​ብ​ኹም፤

Ver Capítulo Cópia de




መዝሙር 76:5
10 Referências Cruzadas  

እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ፤ ተመልከት፤ ስማኝም። የሞት እንቅልፍ እንዳልተኛ ዐይኖቼን አብራ፤


“አሦር የሰው ባልሆነ ሰይፍ ይወድቃል፤ የሥጋ ለባሽ ያልሆነም ሰይፍ ይበላዋል። ከሰይፍ ፊት ይሸሻል፤ ጕልማሶቹም የግዳጅ ሥራ ይሠራሉ።


ከዚያም የእግዚአብሔር መልአክ ወጣ፤ ከአሦራውያን ሰፈር አንድ መቶ ሰማንያ ዐምስት ሺሕ ሰው ገደለ፤ ሰዎቹ ማለዳ ሲነሡ፤ ቦታው ሬሳ በሬሳ ነበር።


እናንተ ልበ ደንዳኖች፣ ከጽድቅም የራቃችሁ ስሙኝ።


ጕረሯቸው በደረቀ ጊዜ ድግስ አዘጋጅላቸዋለሁ፤ እንዲሰክሩም አደርጋቸውና በሣቅ እየፈነደቁ፣ ለዘላለም ላይነቁ ይተኛሉ።” ይላል እግዚአብሔር።


የሰማይ አምላክ የሚያደርገው ሁሉ ትክክል፣ መንገዶቹም ሁሉ ጽድቅ ስለ ሆኑ፣ አሁንም እኔ ናቡከደነፆር እርሱን አወድሰዋለሁ፤ ከፍ ከፍ አደርገዋለሁ፤ አከብረዋለሁም፤ እርሱም በትዕቢት የሚመላለሱትን ማዋረድ ይችላል።


የአሦር ንጉሥ ሆይ፤ እረኞችህ አንቀላፉ፤ መኳንንትህ ዐርፈው ተኙ፤ ሕዝብህ ሰብሳቢ ዐጥተው፣ በተራራ ላይ ተበትነዋል።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios