Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




መዝሙር 71:23 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

23 ዝማሬ በማቀርብልህ ጊዜ ከንፈሮቼ በደስታ ይሞላሉ፤ አንተ የተቤዠሃትም ነፍሴ እልል ትላለች።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

23 ዝማሬን ባቀርብሁልህ ጊዜ ከንፈሮቼ ደስ ይላቸዋል፥ አንተ ያዳንሃትም ነፍሴ እንዲሁ።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

23 ያዳንከኝ እኔ የምስጋና መዝሙር ስዘምርልህ። ከንፈሮቼ የደስታ ጩኸት ይጮኻሉ።

Ver Capítulo Cópia de




መዝሙር 71:23
8 Referências Cruzadas  

ከጕዳትም ሁሉ የታደገኝ መልአክ፣ እርሱ እነዚህን ልጆች ይባርክ፤ እነርሱም በስሜ፣ በአባቶቼ በአብርሃምና በይሥሐቅ ስም ይጠሩ፤ በምድር ላይ እጅግ ይብዙ።”


ዳዊትም ለብኤሮታዊው ለሬሞን ልጆች ለሬካብና ለወንድሙ ለበዓና እንዲህ ሲል መለሰላቸው፤ “ከመከራ ሁሉ ያዳነኝ ሕያው እግዚአብሔርን፣


ሕይወትሽን ከጥፋት ጕድጓድ የሚያድን፣ ምሕረትንና ርኅራኄን የሚያቀዳጅሽ፣


በሕይወት ሳለሁ ለእግዚአብሔር እዘምራለሁ፤ ቆሜ እስከ ሄድሁ ድረስም አምላኬን እወድሳለሁ።


እግዚአብሔር የባሪያዎቹን ነፍስ ይቤዣል፤ እርሱንም መጠጊያ ያደረገ አይፈረድበትም።


ነፍሴ በቅቤና በሥብ እንደሚረካ ሰው ትረካለች፤ አፌም በሚያዜሙ ከንፈሮች በደስታ ያወድስሃል።


እንዲህም እያሉ አዲስ መዝሙር ዘመሩ፤ “መጽሐፉን ልትወስድ፣ ማኅተሞቹንም ልትፈታ ይገባሃል፤ ምክንያቱም ታርደሃል፤ በደምህም ከነገድ ሁሉ፣ ከቋንቋ ሁሉ፣ ከወገን ሁሉ፣ ከሕዝብ ሁሉ ሰዎችን ለእግዚአብሔር ዋጅተሃል።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios