Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




መዝሙር 69:29 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

29 ነገር ግን እኔ በሥቃይና በጭንቅ ላይ እገኛለሁ፤ አምላክ ሆይ፤ ማዳንህ ደግፎ ይያዘኝ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

29 ከሕያዋን መጽሐፍ ይደምሰሱ፥ ከጻድቃንም ጋር አይጻፉ።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

29 እኔ ግን በሥቃይና ተስፋ በመቊረጥ ላይ ስለምገኝ አምላክ ሆይ! ጠብቀኝ፤ አድነኝም።

Ver Capítulo Cópia de




መዝሙር 69:29
17 Referências Cruzadas  

እኔ ድኻና ችግረኛ ነኝና፤ ልቤም በውስጤ ቈስሏልና።


በነፍሱ ላይ ከሚፈርዱት ያድነው ዘንድ፣ እርሱ በችግረኛው ቀኝ በኩል ይቆማልና።


ከጠላቶቼም የሚታደገኝ እርሱ ነው። አንተ ከባላንጦቼ በላይ ከፍ ከፍ አደረግኸኝ፤ ከጨካኞች አዳንኸኝ።


እግዚአብሔር በጭንቅ ቀን ይስማህ፤ የያዕቆብም አምላክ ስም ይጠብቅህ።


እኔ ግን ችግረኛና ድኻ ነኝ፤ ጌታ ግን ያስብልኛል። አንተ ረዳቴና ታዳጊዬም ነህና፤ አምላኬ ሆይ፤ አትዘግይ።


አምላክ ሆይ፤ ከጠላቶቼ እጅ አድነኝ፤ ሊያጠቁኝ ከሚነሡብኝም ጠብቀኝ።


እኔ ግን ችግረኛና ድኻ ነኝ፤ አምላክ ሆይ፤ ፈጥነህ ድረስልኝ፤ አንተ ረዳቴና፣ ታዳጊዬም ነህና፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ አትዘግይ።


እግዚአብሔር ለሙሴ እንዲህ ሲል መለሰለት፤ “የበደለኝን ሁሉ ከመጽሐፌ እደመስሰዋለሁ።


የእስራኤል ተስፋ እግዚአብሔር ሆይ፤ ጥለውህ የሚሄዱ ሁሉ ያፍራሉ፤ ፊታቸውን ከአንተ የሚመልሱ በምድር ውስጥ ይጻፋሉ፤ የሕይወትን ውሃ ምንጭ፣ እግዚአብሔርን ትተዋልና።


ኢየሱስም፣ “ቀበሮዎች ጕድጓድ፣ የሰማይ ወፎችም ጐጆ አላቸው፤ የሰው ልጅ ግን ራሱን የሚያስጠጋበት ቦታ የለውም” ሲል መለሰለት።


የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ጸጋ ታውቃላችሁና፤ በርሱ ድኽነት እናንተ ባለጠጎች ትሆኑ ዘንድ እርሱ ሀብታም ሆኖ ሳለ ለእናንተ ሲል ድኻ ሆነ።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios