Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




መዝሙር 50:4 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 በሕዝቡ ይፈርድ ዘንድ፣ በላይ ያለውን ሰማይንና ምድርን እንዲህ ብሎ ይጠራል፤

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 በላይ ያለውን ሰማይን ምድርንም እንዲሁ በሕዝቡ ለመፍረድ ይጠራል፥

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 በሕዝቡ ላይ ሲፈርድ ሰማይንና ምድርን ለምስክርነት ይጠራል።

Ver Capítulo Cópia de

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 አን​ተን ብቻ በደ​ልሁ፥ በፊ​ት​ህም ክፋ​ትን አደ​ረ​ግሁ፥ በነ​ገ​ርህ ትጸ​ድቅ ዘንድ በፍ​ር​ድ​ህም ታሸ​ንፍ ዘንድ።

Ver Capítulo Cópia de




መዝሙር 50:4
13 Referências Cruzadas  

ሰማያት ጽድቁን ያውጃሉ፤ እግዚአብሔር ራሱ ፈራጅ ነውና። ሴላ


እርሱ ይመጣልና በእግዚአብሔር ፊት ይዘምራሉ፤ በምድር ላይ ሊፈርድ ይመጣል፤ በዓለም ላይ በጽድቅ፣ በሕዝቦችም ላይ በእውነት ይፈርዳል።


እነዚህ በእግዚአብሔር ፊት ይዘምሩ፤ እርሱ በምድር ላይ ሊፈርድ ይመጣልና፤ በዓለም ላይ በጽድቅ፣ በሕዝቦችም ላይ በእውነት ይበይናል።


ሰማያት ሆይ፤ ስሙ! ምድር ሆይ፤ አድምጪ! እግዚአብሔር እንዲህ ሲል ተናግሯልና፤ “ልጆች ወለድሁ፣ አሳደግኋቸውም፤ እነርሱ ግን ዐመፁብኝ።


“ስለዚህ እንደ ገና ከእናንተ ጋራ እፋረዳለሁ፤ ከልጅ ልጆቻችሁም ጋራ እከራከራለሁ።” ይላል እግዚአብሔር።


ሕይወትንና ሞትን፣ በረከትንና ርግማንን በፊትህ እንዳስቀመጥሁ ዛሬ ሰማይንና ምድርን ምስክር አድርጌ እጠራብሃለሁ። እንግዲህ አንተና ልጆችህ በሕይወት እንድትኖሩ ሕይወትን ምረጥ፤


ይህን ቃል ይሰሙ ዘንድ እንድናገር፣ ሰማይንና ምድርን ምስክር አድርጌ እንድጠራባቸው፣ የነገድ አለቆቻችሁን በሙሉና ሹሞቻችሁን ሁሉ በፊቴ ሰብስቡ።


ሰማያት ሆይ፤ አድምጡ፤ እኔም እናገራለሁ፤ ምድር ሆይ፤ አንቺም የአፌን ቃል ስሚ።


ዮርዳኖስን ተሻግራችሁ ከምትወርሷት ምድር ላይ ፈጥናችሁ እንደምትጠፉ በዚህ ቀን ሰማይንና ምድርን በእናንተ ላይ ምስክሮች አድርጌ እጠራለሁ፤ በዚያ ቦታ ብዙ ዘመን አትኖሩም፤ ፈጽሞ ትጠፋላችሁ።


ሊገሥጽህ ድምፁን ከሰማይ እንድትሰማ አደረገ፤ በምድርም ላይ አስፈሪ እሳቱን አሳየህ፤ ከእሳቱም ውስጥ ቃሉን ሰማህ።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios