Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




መዝሙር 48:3 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 እግዚአብሔር በአዳራሾቿ ውስጥ ሆኖ፣ ብርቱ ምሽግ እንደ ሆናት አስመስክሯል።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 በሰሜን በኩል በመልካም ስፍራ የቆመ የምድር ሁሉ ደስታ የጽዮን ተራራ ነው፥ እርሷም የትልቁ ንጉሥ ከተማ ነች።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 እግዚአብሔር በምሽግዋ ውስጥ ነው፤ እርሱም ከለላዋ መሆኑን አስመስክሮአል።

Ver Capítulo Cópia de

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 አፌ ጥበ​ብን ይና​ገ​ራል፥ የል​ቤም ዐሳብ ምክ​ርን፥

Ver Capítulo Cópia de




መዝሙር 48:3
14 Referências Cruzadas  

ይሁን እንጂ ዳዊት የጽዮንን ዐምባ ያዘ፤ ይህችም የዳዊት ከተማ የተባለችው ናት።


እግዚአብሔርም ራሳቸውን እንዳዋረዱ ባየ ጊዜ፣ የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ሲል ወደ ሸማያ መጣ፤ “ራሳቸውን ዝቅ አድርገው ስላዋረዱ እታደጋቸዋለሁ እንጂ አላጠፋቸውም፤ ቍጣዬም በሺሻቅ እጅ በኢየሩሳሌም ላይ አይፈስስም።


በእግዚአብሔር የሚታመኑ፣ ሳትናወጥ ለዘላለም እንደምትኖር እንደ ጽዮን ተራራ ናቸው።


በኢየሩሳሌም የሚኖር እግዚአብሔር፣ ከጽዮን ይባረክ። ሃሌ ሉያ።


የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ከእኛ ጋራ ነው፤ የያዕቆብም አምላክ መጠጊያችን ነው። ሴላ


ፍጹም ውብ ከሆነችው ከጽዮን፣ እግዚአብሔር አበራ።


ውዴ ሆይ፤ አንቺ እንደ ቴርሳ የተዋብሽ፣ እንደ ኢየሩሳሌም ያማርሽ፣ ዐርማቸውን እንደ ያዙ ወታደሮችም ግርማን የተጐናጸፍሽ ነሽ።


በአጠገብሽ የሚያልፉ ሁሉ፣ እጃቸውን ያጨበጭቡብሻል፤ “የውበት መደምደሚያ፣ የምድር ሁሉ ደስታ፣ የተባለች ከተማ ይህች ናትን?” እያሉ ራሳቸውን በመነቅነቅ፣ በኢየሩሳሌም ሴት ልጅ ላይ ያሾፋሉ።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios