Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ማርቆስ 4:16 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 እንዲሁም ሌሎች በጭንጫ መሬት ላይ የተዘራውን ዘር ይመስላሉ፤ ቃሉን በሚሰሙበት ጊዜ ወዲያው በደስታ ይቀበሉታል፤

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 እንዲሁም በጭንጫ ላይ የተዘሩት እነዚህ ናቸው፤ ቃሉንም ሰምተው ወዲያው በደስታ ይቀበሉታል፤

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 እንዲሁም በጭንጫማ ቦታ ላይ የተዘራው የሚያመለክተው ቃሉን ሲሰሙ ወዲያው በደስታ የሚቀበሉትን ሰዎች ነው፤

Ver Capítulo Cópia de

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 እንዲሁም በጭንጫ ላይ የተዘሩት እነዚህ ናቸው፤ ቃሉንም ሰምተው ወዲያው በደስታ ይቀበሉታል፤

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 እንዲሁም በጭንጫ ላይ የተዘሩት እነዚህ ናቸው፥ ቃሉንም ሰምተው ወዲያው በደስታ ይቀበሉታል፥

Ver Capítulo Cópia de




ማርቆስ 4:16
14 Referências Cruzadas  

አንዳንዱም ዘር በቂ ዐፈር በሌለበት በድንጋያማ መሬት ላይ ወደቀ፤ ዐፈሩ ጥልቀት ስላልነበረው ፈጥኖ በቀለ፤


አንዳንድ ሰዎች በመንገድ ላይ የወደቀውን ዘር ይመስላሉ፤ ቃሉን በሚሰሙበት ጊዜ ሰይጣን ወዲያውኑ መጥቶ በውስጣቸው የተዘራውን ቃል ይወስደዋል።


ነገር ግን ሥር ስላልሰደዱ፣ የሚቈዩት ለጥቂት ጊዜ ብቻ ነው፤ በቃሉ ምክንያት መከራ ወይም ስደት በመጣ ጊዜ ወዲያውኑ ይሰናከላሉ።


ምክንያቱም ዮሐንስ ጻድቅና ቅዱስ ሰው መሆኑን ሄሮድስ በማወቁ ይፈራውና ይጠብቀው ነበር። ዮሐንስ የሚናገረውን ሲሰማ ሄሮድስ ቢታወክም በደስታ ያደምጠው ነበር።


በድንጋያማ ቦታ ላይ የወደቀውም ቃሉን ሲሰሙ በደስታ የሚቀበሉ ናቸው፤ እነዚህ ለጊዜው ያምናሉ እንጂ ሥር ስለሌላቸው በፈተና ጊዜ ፈጥነው የሚክዱ ናቸው።


ዮሐንስ እየነደደ ብርሃን የሚሰጥ መብራት ነበረ፤ እናንተም ለጥቂት ጊዜ በብርሃኑ ደስ ልትሠኙ ወደዳችሁ።


አግሪጳም ጳውሎስን፣ “እንዲህ በቀላሉ ክርስቲያን የምታደርገኝ ይመስልሃልን?” አለው።


ራሱ ሲሞን እንኳ ሳይቀር አምኖ ተጠመቀ፤ ፊልጶስንም ተከትሎ ሄደ፤ የሚደረገውን ምልክትና ታላቅ ታምራት አይቶም ተገረመ።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios