Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ሉቃስ 23:4 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 ጲላጦስም ለካህናት አለቆችና ለሕዝቡ፣ “እኔ በዚህ ሰው ላይ ምንም ወንጀል አላገኘሁበትም” አለ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 ጲላጦስም ለካህናት አለቆችና ለሕዝቡ “በዚህ ሰው ላይ ምንም በደል አላገኘሁበትም፤” አለ።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 በዚያን ጊዜ ጲላጦስ ለካህናት አለቆችና ለሕዝቡም “በዚህ ሰው ምንም በደል አላገኘሁበትም” አለ።

Ver Capítulo Cópia de

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 ጲላ​ጦ​ስም ለካ​ህ​ናት አለ​ቆ​ችና ለሕ​ዝቡ፥ “በዚህ ሰው ላይ ያገ​ኘ​ሁት አን​ድስ እንኳ በደል የለም” አላ​ቸው።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 ጲላጦስም ለካህናት አለቆችና ለሕዝቡ፦ በዚህ ሰው አንድ በደል ስንኳ አላገኘሁበትም አለ።

Ver Capítulo Cópia de




ሉቃስ 23:4
13 Referências Cruzadas  

በፍርድ ወንበር ላይ ተቀምጦ ሳለ ሚስቱ፣ “በርሱ ምክንያት ዛሬ በሕልም ብዙ ስለ ተሠቃየሁ፣ በዚያ ንጹሕ ሰው ላይ ምንም ነገር እንዳታደርግ” የሚል መልእክት ላከችበት።


ጲላጦስም፣ “ለምን? ምን የፈጸመው ወንጀል አለ” አላቸው። እነርሱ ግን፣ “ስቀለው!” እያሉ የባሰ ጮኹ።


ጲላጦስም ሦስተኛ ጊዜ፣ “ለምን? ይህ ሰው ምን የፈጸመው ወንጀል አለ? እኔ ለሞት የሚያበቃ ምንም በደል አላገኘሁበትም፤ ስለዚህ ቀጥቼ እፈታዋለሁ” አላቸው።


ጲላጦስም፣ “እውነት ምንድን ነው?” አለው፤ ይህን ከተናገረ በኋላም እንደ ገና ወደ አይሁድ ወጥቶ እንዲህ አላቸው፤ “እኔ የሚያስከስስ በደል አላገኘሁበትም፤


እኔም ለሞት የሚያበቃ አንዳች ነገር አለማድረጉን ተረዳሁ፤ ሆኖም ወደ ንጉሠ ነገሥቱ ይግባኝ በማለቱ ወደ ሮም ልልከው ወሰንሁ።


የአባቶቻችን አምላክ፣ የአብርሃም አምላክ፣ የይሥሐቅ አምላክ፣ የያዕቆብ አምላክ ብላቴናውን ኢየሱስን አከበረው፤ እናንተ ግን እንዲሞት አሳልፋችሁ ሰጣችሁት፤ ጲላጦስ ሊፈታው ቢፈልግም እናንተ በርሱ ፊት ካዳችሁት፤


እንግዲህ ለእኛ የሚያስፈልገን፣ ቅዱስ፣ ነቀፋ የሌለበት፣ ንጹሕ፣ ከኀጢአተኞች የተለየና ከሰማያት በላይ የከበረ እንደዚህ ያለ ሊቀ ካህናት ነው።


ነገር ግን እናንተ የተዋጃችሁት ነውርና እንከን እንደሌለበት በግ ደም፣ በክርስቶስ ክቡር ደም ነው።


“እርሱ ኀጢአት አላደረገም፤ በአፉም ተንኰል አልተገኘበትም።”


እንዲሁም ክርስቶስ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ስለ ኀጢአት ሞቷልና፤ ወደ እግዚአብሔር ያቀርባችሁ ዘንድ ጻድቅ የሆነው እርሱ ስለ ዐመፀኞች ሞተ፤ እርሱ በሥጋ ሞተ፤ በመንፈስ ግን ሕያው ሆነ፤


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios