Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ኢያሱ 7:17 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 የይሁዳንም ጐሣዎች ወደ ፊት አቀረበ፤ ከእነዚህም የዛራን ጐሣ ለየ፤ እነዚህን ደግሞ በየቤተ ሰባቸው እንዲወጡ አደረገ፤ ከእነዚህም ዘንበሪ ተለየ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 የይሁዳንም ወገን አቀረበ የዛራንም ወገን ለየ፤ የዛራንም ወገን ሰዎች አንድ በአንድ አቀረበ፤ ዘንበሪም ተለየ፤

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 ኢያሱም የይሁዳን ነገድ በየጐሣው አቀረበ፤ ከዚያም በኋላ የዛራሕ ጐሳ ለብቻው ተለየ፤ የዛራሕንም ጐሣ በየቤተሰቡ አቀረበው፤ የዛብዲም ቤተሰብ ለብቻው ተለየ፤

Ver Capítulo Cópia de

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 የይ​ሁ​ዳም ወገ​ኖች ተለዩ፤ በዛ​ራም ወገን ምል​ክት ታየ፤ የዛ​ራም ወገን በየ​ቤተ ሰቡ ተለየ፤

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 የይሁዳንም ወገን አቀረበ የዛራንም ወገን ለየ፥ የዛራንም ወገን ሰዎች አቀረበ፥

Ver Capítulo Cópia de




ኢያሱ 7:17
6 Referências Cruzadas  

ከዚያ በኋላ እጁ ላይ ቀይ ክር የታሰረለት ወንድሙ ተወለደ፤ ስሙም ዛራ ተባለ።


በዛራ በኩል፣ የዛራውያን ጐሣ፤ በሳኡል በኩል፣ የሳኡላውያን ጐሣ፤


የይሁዳ ዘሮች በየጐሣቸው እነዚህ ነበሩ፤ በሴሎም በኩል፣ የሴሎማውያን ጐሣ፤ በፋሬስ በኩል፣ የፋሬሳውያን ጐሣ፤ በዛራ በኩል፣ የዛራውያን ጐሣ፤


በማግስቱም ጧት ኢያሱ ማልዶ ተነሣ፤ እስራኤልንም በየነገድ በየነገዳቸው ሆነው እንዲቀርቡ አደረገ፤ ከዚያም የይሁዳ ነገድ ተለየ።


ኢያሱ የዘንበሪን ቤተ ሰብ አባላት አንድ በአንድ ወደ ፊት እንዲቀርቡ አደረገ፤ ከዚያም ከይሁዳ ነገድ የሆነውም የዛራ ልጅ፣ የዘንበሪ ልጅ፣ የከርሚ ልጅ አካን ለብቻው ተለየ።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios