Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ኢያሱ 12:8 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 ይህም ተራራማው አገር፤ በስተምዕራብ ያለው የኰረብታ ግርጌ፣ ዓረባ፣ የተራራው ሸንተረሮች፣ ምድረ በዳውና ኔጌብ ማለት የኬጢያውያን፣ የአሞራውያን፣ የከነዓናውያን፣ የፌርዛውያን፣ የኤዊያውያንና የኢያቡሳውያን ምድር ነው። ነገሥታቱም እነዚህ ናቸው፤

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 በተራራማው አገር፥ በቈላውም፥ በዓረባም፥ በቁልቁለቱም፥ በምድረ በዳውም፥ በደቡቡም ያሉ ኬጢያውያን አሞራውያንም ከነዓናውያንም ፌርዛውያንም ኤዊያውያንም ኢያቡሳውያንም ዘንድ ነበር።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 ይህም የርስት ድርሻ ኮረብታማውን አገር በስተ ምዕራብ ያለውን የኮረብታ ግርጌ፥ የዮርዳኖስን ሸለቆና በእርሱም ኮረብታዎች ግርጌ ያሉትን በስተ ምሥራቅ በኩል የሚገኘውን ረባዳ ቦታና በደቡብ በኩል የሚገኘውን በረሓማ ምድር ሁሉ ያጠቃልል ነበር፤ ይህም ምድር ቀድሞ የሒታውያን፥ የአሞራውያን፥ የከነዓናውያን፥ የፈሪዛውያን፥ የሒዋውያንና የኢያቡሳውያን መኖሪያ ነበር።

Ver Capítulo Cópia de

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 በተ​ራ​ራና በሜዳ በዓ​ረባ፥ በአ​ሴ​ዶት በቆ​ላው፥ በና​ጌብ፥ በኬ​ጤ​ዎ​ንና በአ​ሞ​ሬ​ዎን፥ በከ​ና​ኔ​ዎ​ንና በፌ​ር​ዜ​ዎን፥ በኢ​ያ​ቡ​ሴ​ዎ​ንና በኤ​ዌ​ዎን ያለ ርስ​ታ​ቸ​ውን አወ​ረ​ሳ​ቸው።

Ver Capítulo Cópia de




ኢያሱ 12:8
14 Referências Cruzadas  

የኤዊያውያን፣ የዐርካውያን፣ የሲኒውያን፣


አብራምም ከዚያ ተነሥቶ ወደ ኔጌብ ሄደ።


ይህም በመሆኑ በአብራምና በሎጥ መንጎች እረኞች መካከል ጠብ ተፈጠረ። በዚያ ዘመን ከነዓናውያንና ፌርዛውያን በዚያው አገር ይኖሩ ነበር።


መልአኬ በፊትህ ይሄዳል፤ አንተንም ወደ አሞራውያን፣ ወደ ኬጢያውያን፣ ወደ ፌርዛውያን፣ ወደ ከነዓናውያን፣ ወደ ኤዊያውያንና ኢያቡሳውያን ምድር ያስገባሃል፤ እኔም እነርሱን አጠፋቸዋለሁ።


ስለዚህም ከግብጻውያን እጅ ልታደጋቸውና ማርና ወተት ወደምታፈስሰው ሰፊና ለም ወደሆነችው ወደ ከነዓናውያን፣ ኬጢያውያን፣ አሞራውያን፣ ፌርዛውያን፣ ኤዊያውያንና ኢያቡሳውያን ምድር ላወጣቸው ወርጃለሁ።


አምላክህ እግዚአብሔር ልትወርሳት ወደምትገባባት ምድር በሚያመጣህና ብዙዎችን ከአንተ የሚበልጡ ታላላቆችና ብርቱዎች የሆኑትን ሰባቱን አሕዛብ፦ ኬጢያውያንን፤ ጌርጌሳውያንን፣ አሞራውያንን፣ ከነዓናውያንን፣ ፌርዛውያንን፣ ኤዊያውያንንና ኢያቡሳውያንን ከፊትህ በሚያስወጣቸው ጊዜ፣


እስራኤል ሆይ፤ ስማ፤ ሰማይ ጠቀስ ቅጥር ያላቸው ታላላቅ ከተሞች ያሏቸውን፣ ከአንተ ይልቅ ታላቅና ብርቱ የሆኑትን አሕዛብ አስለቅቀህ ለመግባት ዮርዳኖስን አሁን ትሻገራለህ።


በዚህ ሁኔታም ኢያሱ ተራራማውን አገር ኔጌብን፣ የምዕራቡን ቈላና የተራራውን ሸንተረሮች ጨምሮ ምድሪቱን በሙሉ ከነገሥታቷ ጋራ ያዘ። የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ባዘዘውም መሠረት፣ እስትንፋስ ያላቸውን ሁሉ ፈጽሞ ደመሰሰ፤ ማንንም በሕይወት አላስቀረም።


ኢያሱ ያን ምድር በሙሉ፣ ማለት ተራራማውን አገር፣ ኔጌብን ሁሉ፣ የጎሶምን ምድር በሙሉ፣ የምዕራቡን ቈላ፣ ዓረባን እንዲሁም የእስራኤልን አገር ደጋውንና ቈላውን ጠቅልሎ ያዘ፤


እንግዲህ ሕያው አምላክ በመካከላችሁ መሆኑንና እርሱም በርግጥ ከነዓናውያንን፣ ኬጢያውያንን፣ ኤዊያውያንን፣ ፌርዛውያንን፣ ጌርጌሳውያንን፣ አሞራውያንንና ኢያቡሳውያንን ከፊታችሁ እንዴት አድርጎ እንደሚያሳድዳቸው የምታውቁት በዚህ ነው።


በዮርዳኖስ ምዕራብ ባለው በተራራማው አገር፣ በቈላማው ምድር እንዲሁም እስከ ሊባኖስ በሚደርሰው በመላው በታላቁ ባሕር ዳርቻ የነበሩት የኬጢያውያን፣ የአሞራውያን፣ የከነዓናውያን፣ የፌርዛውያን፣ የኤዊያውያን፣ የኢያቡሳውያን ነገሥታት ይህን በሰሙ ጊዜ፣


ከዚያም በኋላ የይሁዳ ሰዎች በኰረብታማው አገር፣ በኔጌብና በምዕራቡ ኰረብታ ግርጌ የሚኖሩትን ከነዓናውያንን ለመውጋት ወረዱ፤


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios