Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ዘፍጥረት 4:21 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 ወንድሙም ዩባል ይባላል፤ እርሱም የበገና ደርዳሪዎችና የዋሽንት ነፊዎች አባት ነበረ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 የወንድሙም ስም ዩባል ነበረ፥ እርሱም በገናንና ዋሽንትን ለሚይዙ አባት ነበረ።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 የእርሱ ወንድም ዮባልም ዋሽንትና በገና የሚጫወቱ የሙዚቀኞች አባት ነበር።

Ver Capítulo Cópia de

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 የወ​ን​ድ​ሙም ስም ኢዮ​ቤል ነበር፤ እር​ሱም በገ​ና​ንና መሰ​ን​ቆን አስ​ተ​ማረ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 የወንድሙም ስም ዩባል ነበረ፤ እርሱም በገናንና መለከትን ለሚይዙ አባት ነበረ።

Ver Capítulo Cópia de




ዘፍጥረት 4:21
8 Referências Cruzadas  

ለመሆኑ ለምን ተደብቀህ ሄድህ? ለምንስ አታለልኸኝ? ብትነግረኝ ኖሮ፣ በደስታና በዘፈን በከበሮና በበገና አልሸኝህም ነበር?


ዓዳ ያባልን ወለደች፤ እርሱም በድንኳን ለሚኖሩ ከብት አርቢዎች አባት ነበረ።


ሴላም ደግሞ ቱባልቃይን የተባለ ወንድ ልጅ ነበራት፤ እርሱም ከብረትና ከናስ ልዩ ልዩ መሣሪያዎችን እየቀረጸ የሚሠራ ነበር። የቱባልቃይን እኅት ናዕማ ትባል ነበር።


በከበሮና በክራር ይዘፍናሉ፤ በዋሽንትም ድምፅ ይፈነጫሉ።


በከበሮና በሽብሸባ አመስግኑት፤ በባለአውታር መሣሪያና በእንቢልታ አመስግኑት።


በግብዣቸው ላይ በገናና መሰንቆ፣ ከበሮና ዋሽንት እንዲሁም የወይን ጠጅ አለ፤ ነገር ግን ለእግዚአብሔር ሥራ ቦታ አልሰጡም፤ ለእጆቹም ሥራ ክብር አላሳዩም።


ባልተቃኘ በገና እንደ ዳዊት ለምትዘፍኑ፣ በሙዚቃ መሣሪያ ለመጫወት ለምትሹ፣


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios