Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ዘፍጥረት 38:5 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 አሁንም ደግማ ወንድ ልጅ ወለደች፤ ስሙንም ሴሎም ብላ አወጣችለት፤ እርሱንም የወለደችው ክዚብ በተባለ ቦታ ነበር።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 አሁንም ደግማ ወንድ ልጅ ወለደች፤ ስሙንም ሴሎም ብላ አወጣችለት፤ እርሱንም የወለደችው ክዚብ በተባለ ቦታ ነበር።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 እንደገናም ወንድ ልጅ ወለደች ስሙንም ሴላ ብላ ጠራችው፤ እርሱንም የወለደችው ይሁዳ አክዚብ በሚባል ቦታ በሚኖርበት ጊዜ ነው።

Ver Capítulo Cópia de

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 እን​ደ​ገና ደግሞ ወንድ ልጅን ወለ​ደች፤ ስሙ​ንም ሴሎም ብላ ጠራ​ችው፤ እነ​ር​ሱ​ንም በወ​ለ​ደች ጊዜ ኬሴቢ በሚ​ባል ሀገር ነበ​ረች።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 እንደ ገና ደግሞ ወንድ ልጅን ወለደች ስሙንም ሴሎም ብላ ጠራችው እርሱንም በወለደች ጊዜ ክዚብ በሚባል አገር ነበረች።

Ver Capítulo Cópia de




ዘፍጥረት 38:5
8 Referências Cruzadas  

ከዚያም ይሁዳ ምራቱን ትዕማርን፣ “ልጄ ሴሎም ለአካለ መጠን እስኪደርስ ድረስ ወደ አባትሽ ቤት ሄደሽ መበለት ሆነሽ ብትኖሪ ይሻላል” አላት። ይህን ያለውም፣ ሴሎም እንደ ወንድሞቹ ተቀሥፎ ይሞትብኛል ብሎ ስለ ሠጋ ነበር። ትዕማርም እንዳላት ሄደች፤ በአባቷም ቤት ተቀመጠች።


ይሁዳም ዕቃዎቹን ዐውቆ፣ “ልጄ ሴሎም እንዲያገባት ባለማድረጌ፣ እርሷ ከእኔ ይልቅ ትክክል ናት” አለ። ከዚያም በኋላ ከርሷ ጋራ አልተኛም።


ይሁዳ የበኵር ልጁን ዔርን፣ ትዕማር የምትባል ሚስት አጋባው።


የይሁዳ ልጆች፦ ዔር፣ አውናን፣ ሴሎም፣ ፋሬስ እና ዛራ ናቸው። ነገር ግን ዔርና አውናን በከነዓን ምድር ሞቱ። የፋሬስ ልጆች፦ ኤስሮምና ሐሙል ናቸው።


የይሁዳ ወንዶች ልጆች፤ ዔር፣ አውናን፣ ሴሎም፤ እነዚህን ሦስቱን ከከነዓናዊት ሚስቱ ከሴዋ ወለደ። የበኵር ልጁ ዔር በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ሰው ሆነ፤ እግዚአብሔርም ቀሠፈው።


የይሁዳ ልጅ የሴሎም ወንዶች ልጆች፤ የሌካ አባት ዔር፣ የመሪሳና በቤት አሽቤዓ የበፍታ ጨርቅ ሠሪ የሆኑት ጐሣዎች አባት ለዓዳ፣


ዔርና አውናን የይሁዳ ልጆች ነበሩ፤ ነገር ግን በከነዓን ምድር ሞተዋል።


የይሁዳ ዘሮች በየጐሣቸው እነዚህ ነበሩ፤ በሴሎም በኩል፣ የሴሎማውያን ጐሣ፤ በፋሬስ በኩል፣ የፋሬሳውያን ጐሣ፤ በዛራ በኩል፣ የዛራውያን ጐሣ፤


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios