Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ዘፍጥረት 20:12 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 ደግሞም እኮ በርግጥ እኅቴ ናት፤ ከአንድ እናት ባንወለድም በአባት አንድ ነን፤ ኋላም አገባኋት።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 እርሷም ደግሞ በእውነት እኅቴ ናት፥ የእናቴ ልጅ አይደለችም እንጂ የአባቴ ልጅ ናት፥ ለእኔም ሚስት ሆነች።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 ደግሞም እርስዋ የአባቴ ልጅ ስለ ሆነች በእርግጥ እኅቴ ናት፤ ነገር ግን የእናቴ ልጅ ስላልሆነች አገባኋት።

Ver Capítulo Cópia de

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 እር​ስ​ዋም ደግሞ በእ​ናቴ ወገን አይ​ደ​ለ​ችም እንጂ በእ​ው​ነት በአ​ባቴ ወገን እኅቴ ናት፤ ለእ​ኔም ሚስት ሆነች።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 እርስዋም ደግሞ በእውነት እኅቴ ናት የእናቴ ልጅ አይደለችም እንጂ የአባቴ ልጅ ናት ለእኔም ሚስት ሆነች።

Ver Capítulo Cópia de




ዘፍጥረት 20:12
8 Referências Cruzadas  

አብራምና ናኮር ሁለቱም ሚስት አገቡ፤ የአብራም ሚስት ሦራ ስትባል፣ የናኮር ሚስት ደግሞ ሚልካ ትባል ነበር፤ ሚልካም የሐራን ልጅ ናት፤ ሐራንም የሚልካና የዮስካ አባት ነበረ።


ስለዚህ ለአንቺ ሲሉ እንዲንከባከቡኝ፣ ሕይወቴም እንድትተርፍ፣ ‘እኅቱ ነኝ’ በዪ።”


አብርሃምም አቢሜሌክን እንዲህ አለው፤ “ ‘እዚህ ቦታ ፈሪሀ እግዚአብሔር አለመኖሩን ተገነዘብሁ፤ ሰዎቹም ለሚስቴ ሲሉ ይገድሉኛል’ ብዬ ሠጋሁ፤


እግዚአብሔር አዝዞኝ ከአባቴ ቤት ወጥቼ በየአገሩ ስዞር፣ ‘ለእኔ ያለሽን ፍቅር በዚህ ግለጭልኝ፤ በየደረስንበት ስፍራ ሁሉ “እርሱ ወንድሜ ነው” በዪ’ ብያት ነበር።”


በዚያም አብርሃም ሚስቱን ሣራን፣ “እኅቴ ናት” ይል ነበር። ስለዚህ የጌራራ ንጉሥ አቢሜሌክ መልእክተኛ ልኮ ሣራን ወሰዳት።


የዚያም አገር ሰዎች ስለ ሚስቱ በጠየቁት ጊዜ፣ “እኅቴ ናት” አለ፤ ምክንያቱም፣ “ሚስቴ ናት ብል ርብቃ ቈንጆ ስለ ሆነች፣ ያገሬው ሰዎች በርሷ ምክንያት ይገድሉኛል” በማለት ፈርቶ ነበር።


እኔስ እንዴት እሆናለሁ? ነውሬንስ ተሸክሜ የት እገባለሁ? አንተስ ብትሆን በእስራኤል ሞኞች እንደ አንዱ መቈጠርህ አይደለምን? እባክህ ለንጉሡ ንገረው፤ እንዳላገባህም አይከለክለኝም።”


ከማንኛውም ዐይነት ክፉ ነገር ራቁ።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios