Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ዘፍጥረት 18:7 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 ከዚያም ወደ መንጋው በጥድፊያ ሄዶ፣ አንድ ፍርጥም ያለ ሥጋው ገር የሆነ ጥጃ መርጦ ለአገልጋዩ ሰጠው፤ አገልጋዩም ጥጃውን ዐርዶ አዘጋጀው።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 አብርሃምም ወደ ላሞቹ ሮጠ፥ እጅግ የሰባም ታናሽ ጥጃ ያዘና ለብላቴናው ሰጠው፥ ያዘጋጅም ዘንድ ተቻኰለ።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 ከዚህ በኋላ አብርሃም ወደ መንጋው ሄደና ለግላጋውንና መልካሙን ጥጃ መርጦ ለአገልጋዩ ሰጠው፤ አገልጋዩም በፍጥነት ዐርዶ አወራርዶ አዘጋጀው፤

Ver Capítulo Cópia de

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 አብ​ር​ሃ​ምም ወደ ላሞቹ ሮጠ፤ እጅግ የሰ​ባም ታናሽ ጥጃ ያዘና ለብ​ላ​ቴ​ናው ሰጠው፤ ያዘ​ጋ​ጅም ዘንድ ተቻ​ኮለ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 አብርሃምም ወደ ላሞቹ ሮጠ እጅግ የሰባም ታናሽ ጥጃ ያዘና ለብላቴንው ስጠው፥ ያዘጋጅም ዘንድ ተቻኮለ።

Ver Capítulo Cópia de




ዘፍጥረት 18:7
11 Referências Cruzadas  

አብርሃም በፍጥነት ሣራ ወዳለችበት ወደ ድንኳኑ ገብቶ፣ “ቶሎ ብለሽ ሦስት መስፈሪያ ስልቅ ዱቄት አቡኪና ቂጣ ጋግሪ” አላት።


አብርሃምም ርጎ፣ ወተትና የተዘጋጀውን የጥጃ ሥጋ አቀረበላቸው፤ ሲበሉም ዛፉ ሥር አጠገባቸው ቆሞ ነበር።


ሎጥ ግን አጥብቆ ስለ ለመናቸው ዐብረውት ወደ ቤቱ ገቡ፤ ከዚያም ቂጣ ጋግሮ አቀረበላቸውና በሉ።


በዝኆን ጥርስ ባጌጠ ዐልጋ ላይ ለምትተኙ፤ በድንክ ዐልጋችሁ ላይ ለምትዝናኑ፣ ከበጎች መንጋ ጠቦትን፣ ከሠቡትም ጥጃን ለምትበሉ፤


“በመንጋው ውስጥ ተቀባይነት ያለው ተባዕት በግ ኖሮት ይህንኑ ሊሰጥ ተስሎ ሳለ፣ በማታለል ነውር ያለበትን እንስሳ ለጌታ የሚሠዋ ርጉም ይሁን፤ እኔ ታላቅ ንጉሥ ነኝ፤ ስሜም በሕዝቦች ዘንድ ሊፈራ የሚገባ ነውና” ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር።


“እንደ ገናም ሌሎች ባሮች ልኮ፣ ‘የተጋበዙትን፣ እነሆ፣ በሬዎችንና የሠቡ ከብቶቼን ዐርጄ ድግሱን አዘጋጅቻለሁ፤ ሁሉም ነገር ዝግጁ ስለ ሆነ፣ ወደ ሰርጉ ኑ በሏቸው’ አለ።


የሠባውንም ፍሪዳ አምጡና ዕረዱ፤ እንብላ፤ እንደሰት፤


አገልጋዩም፣ ‘ወንድምህ መጥቷል፤ በሰላም በጤና ስለ መጣም አባትህ የሠባውን ፍሪዳ ዐርዶለታል’ አለው።


ነገር ግን ይህ ልጅህ ንብረትህን ከጋለሞቶች ጋራ አውድሞ ሲመጣ፣ የሠባውን ፍሪዳ ዐረድህለት።’


ሴትዮዋም በቤቷ የሠባ ጥጃ ስለ ነበራት፣ ፈጥና ዐረደችው፤ ዱቄት ወስዳ ለወሰች፣ ቂጣም ጋገረች።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios