Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ዘፍጥረት 18:30 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

30 ደግሞም አብርሃም፣ “ጌታዬ አይቈጣ፤ እባክህ ልናገር፤ ሠላሳ ጻድቃን ብቻ ቢገኙስ?” እርሱም፣ “ሠላሳ ባገኝ አላጠፋትም” ብሎ መለሰ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

30 እርሱም፦ “ጌታዬ አይቆጣ እኔም እናገራለሁ ምናልባት ከዚያ ሠላሳ ቢገኙሳ?” አለ። እርሱም፦ “ከዚያ ሰላሳ ባገኝ አላጠፋም” አለ።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

30 አብርሃምም “ጌታ ሆይ፥ እባክህ አትቈጣ፤ እንደገና ልናገር፤ ምናልባት ሠላሳ ብቻ ቢገኙስ?” አለ። እግዚአብሔርም “ሠላሳ ቢገኙ ለእነርሱ ስል ከተማይቱን አላጠፋም” አለ።

Ver Capítulo Cópia de

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

30 አብ​ር​ሃ​ምም እን​ደ​ገና ነገ​ሩን ደገመ፤ እን​ዲ​ህም አለው፥ “ከዚያ ሠላሳ ቢገ​ኙሳ?” እር​ሱም፥ “ስለ ሠላ​ሳው አላ​ጠ​ፋ​ትም” አለው።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

30 እርሱም ጌታዬ አይቆጣ እኔም እናገራለሁ ምናልባት ከዚያ ሠላሳ ባገኝ አላጠፋም አለ።

Ver Capítulo Cópia de




ዘፍጥረት 18:30
12 Referências Cruzadas  

አብርሃምም እንደ ገና፣ “ምናልባት አርባ ጻድቃን ቢገኙስ?” አለ። እርሱም፣ “ለአርባው ስል እምራታለሁ” አለ።


አብርሃምም፣ “ከጌታዬ ጋራ እናገር ዘንድ መቼም አንዴ ደፍሬአለሁና ምናልባት ሃያ ብቻ ቢገኙስ?” አለ። እርሱም፣ “ሃያ ቢገኙ፣ ለእነርሱ ስል እምራታለሁ” አለ።


ይሁዳም ወደ ዮሴፍ ቀረብ ብሎ፣ “ጌታዬ ሆይ፤ እኔ አገልጋይህ አንዲት ቃል ብቻ ልናገር፤ አንተም የፈርዖንን ያህል የተከበርህ ስለ ሆንህ፣ እባክህን እኔን አገልጋይህን አትቈጣኝ።


“እኔ ከንቱ ሰው፣ ምን እመልስልሃለሁ? እጄን በአፌ ላይ እጭናለሁ።


እግዚአብሔር ሆይ፤ የተገፉትን ምኞት ትሰማለህ፤ ልባቸውን ታበረታለህ፤ ጆሮህንም ወደ እነርሱ ጣል ታደርጋለህ፤


እግዚአብሔር በቅዱሳን ጉባኤ መካከል በጣም የሚፈራ፣ በዙሪያውም ካሉት ሁሉ በላይ እጅግ የሚከበር ነው።


ደም ተበቃዩ ዐስቧቸዋልና፤ የጭቍኖችንም ጩኸት አልዘነጋም።


እኔም፣ “ከንፈሮቼ የረከሱብኝ ሰው ነኝ፤ የምኖረውም ከንፈሮቹ በረከሱበት ሕዝብ መካከል ነው፤ ዐይኖቼም ንጉሡን፣ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔርን አይተዋልና ጠፍቻለሁ፣ ወዮልኝ!” አልሁ።


ከዚያም ጌዴዎን እግዚአብሔርን እንዲህ አለው፤ “እባክህ አትቈጣኝ፤ አንዲት ጥያቄ እንደ ገና ልጠይቅ። በጠጕሩ ባዘቶ ላይ ሌላ ሙከራ እንዳደርግ ፍቀድልኝ፤ በዚህ ጊዜ ምድሩ ሁሉ በጤዛ ተሸፍኖ ባዘቶው ደረቅ ይሁን።”


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios