Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ዘፍጥረት 11:8 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 ስለዚህ እግዚአብሔር በምድር ሁሉ ላይ በታተናቸው፤ ከተማዋንም መሥራት አቆሙ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 ከዚያ በኋላ ጌታ በምድር ሁሉ ላይ በተናቸው፥ ከተማይቱንም መሥራት አቆሙ።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር በምድር ሁሉ ላይ በተናቸው፤ ከተማውንም መሥራት አቆሙ፤

Ver Capítulo Cópia de

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቋን​ቋ​ቸ​ውን ለያየ፤ ከዚ​ያም በም​ድር ፊት ሁሉ ላይ በተ​ና​ቸው፤ ከዚ​ያም በኋላ ከተ​ማ​ዪ​ቱ​ንና ግን​ቡን መሥ​ራ​ትን ተዉ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 እግዚአብሔርም ከዚያ በምድር ሁሉ ላይ በተናቸው፤ ከተማይቱንም መሥራት ተው።

Ver Capítulo Cópia de




ዘፍጥረት 11:8
10 Referências Cruzadas  

ለዔቦርም ሁለት ወንዶች ልጆች ተወለዱለት፤ አንደኛው ልጅ በዘመኑ ምድር ተከፍላ ስለ ነበር ፋሌቅ ተባለ፤ ወንድሙም ዮቅጣን ተባለ።


የኖኅ ወንዶች ልጆች ጐሣዎች እንደ ትውልዳቸው በየነገዳቸው እነዚህ ነበሩ። ከጥፋት ውሃ በኋላ ሕዝቦች በምድር ላይ የተሠራጩት ከእነዚሁ ነው።


ከእነዚህም በየነገዳቸው፣ በየጐሣቸውና በየቋንቋቸው ተከፋፍለው በባሕር ዳርና በደሴቶች፣ በየምድራቸው የሚኖሩ ሕዝቦች ወጡ።


ከዚያም “ለስማችን መጠሪያ እንዲሆንና በምድር ላይ እንዳንበተን፣ ኑ፤ ከተማ፣ ሰማይ የሚደርስ ግንብም ለራሳችን እንሥራ” አሉ።


እግዚአብሔር በዚያ የመላውን ዓለም ቋንቋ ስለ ደበላለቀ የከተማዪቱ ስም ባቤል ተባለ። ከዚያም እግዚአብሔር ሰዎቹን በምድር ሁሉ በተናቸው።


እጅግ አስፈሪ የሆነ ቍጣቸው፣ ጭከና የተሞላ ንዴታቸው የተረገመ ይሁን፤ በያዕቆብ እበትናቸዋለሁ፤ በመላው እስራኤልም አሠራጫቸዋለሁ።


እግዚአብሔር የሕዝቦችን ምክክር ከንቱ ያደርጋል፤ የሕዝብንም ዕቅድ ያጨናግፋል።


ጠላቶችህ እግዚአብሔር ሆይ፤ ጠላቶችህ ይጠፋሉና፤ ክፉ አድራጊዎችም ሁሉ ይበተናሉ።


በክንዱ ብርቱ ሥራ ሠርቷል፤ በልባቸው ሐሳብ የሚታበዩትን በትኗቸዋል፤


ልዑል ለአሕዛብ ርስታቸውን በሰጠ ጊዜ፣ የሰውንም ዘር በለያየ ጊዜ፣ በእስራኤል ልጆች ቍጥር ልክ፣ የአሕዛብን ርስት ድንበር ለየ፤


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios