Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ዘዳግም 10:1 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 በዚያ ጊዜ እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ፤ “እንደ መጀመሪያዎቹ ያሉ ሁለት የድንጋይ ጽላት ቀርጸህ ወደ እኔ ወደ ተራራው ላይ ውጣ፤ ታቦትም ከዕንጨት ሥራ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 በዚያን ጊዜ ጌታ እንዲህ አለኝ፥ “እንደ ቀድሞ ዓይነት ሁለት የድንጋይ ጽላቶች ጠርበህ ወደ እኔ ወደ ተራራው ውጣ፥ ለአንተም የእንጨት ታቦት ሥራ።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ፤ “ቀድሞ የተሰበሩትን የድንጋይ ጽላቶች አስመስለህ በምትካቸው ሁለት ጽላቶች ቅረጽ፤ ለእነርሱ ማኖሪያ የሚሆን ታቦትም ከእንጨት ሥራ፤ እኔም ወዳለሁበት ተራራ ውጣ፤

Ver Capítulo Cópia de

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 “በዚ​ያን ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ፊተ​ኞች ያሉ​ትን ሁለት የድ​ን​ጋይ ጽላት ለአ​ንተ ቀር​ፀህ ወደ እኔ ወደ ተራ​ራው ውጣ፤ ለአ​ን​ተም የእ​ን​ጨት ታቦት ሥራ፤

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 በዚያን ጊዜ እግዚአብሔር፦ እንደ ፊተኞች ያሉትን ሁለት የድንጋይ ጽላቶች ጠርበህ ወደ እኔ ወደ ተራራው ውጣ፥ ለአንተም የእንጨት ታቦት ሥራ፤

Ver Capítulo Cópia de




ዘዳግም 10:1
5 Referências Cruzadas  

ስለዚህ ሙሴ እንደ መጀመሪያዎቹ ያሉ ሁለት የድንጋይ ጽላት ጠርቦ፣ እግዚአብሔር እንዳዘዘው በማለዳ ወደ ሲና ተራራ ወጣ፤ ሁለቱን የድንጋይ ጽላትም በእጆቹ ያዘ።


በዚያም ውስጥ የወርቅ ማዕጠንትና በወርቅ የተለበጠው የኪዳኑ ታቦት ነበሩ፤ ይህም ታቦት መና ያለበትን የወርቅ መሶብ፣ የለመለመችውን የአሮንን በትርና ኪዳኑ የተጻፈበትን ጽላት ይዟል።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios