Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ዘካርያስ 7:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 ዳርዮስ በነገሠ በአራተኛው ዓመት፥ ኪስሌው የተባለ ዘጠነኛው ወር በገባ በአራተኛው ቀን እግዚአብሔር ለዘካርያስ የነገረው ቃል ይህ ነው፤

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 ዳርዮስ በነገሠ በአራተኛው ዓመት፣ ካሴሉ በተባለው በዘጠነኛው ወር፣ በአራተኛው ቀን የእግዚአብሔር ቃል ወደ ዘካርያስ እንዲህ ሲል መጣ፤

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 በንጉሡም በዳርዮስ በአራተኛው ዓመት፥ ካሴሉ በሚባል በዘጠነኛው ወር በአራተኛው ቀን፥ የጌታ ቃል ወደ ዘካርያስ መጣ።

Ver Capítulo Cópia de

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 በንጉሡም በዳርዮስ በአራተኛው ዓመት ካሴሉ በሚባል በዘጠነኛው ወር በአራተኛው ቀን የእግዚአብሔር ቃል ወደ ዘካርያስ መጣ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 በንጉሡም በዳርዮስ በአራተኛው ዓመት ካሴሉ በሚባል በዘጠነኛው ወር በአራተኛው ቀን የእግዚአብሔር ቃል ወደ ዘካርያስ መጣ።

Ver Capítulo Cópia de




ዘካርያስ 7:1
6 Referências Cruzadas  

የሐካልያ ልጅ ነህምያ የተናገረው ቃል ይህ ነው፦ አርጤክስስ የፋርስ ንጉሠ ነገሥት በሆነ በሃያኛው ዓመት ኪስሌው ተብሎ በሚጠራው ወር እኔ ነህምያ ዋና ከተማ በሆነችው በሱሳ ውስጥ ነበርኩ።


ዳርዮስ በነገሠ በሁለተኛው ዓመት ዘጠነኛው ወር በገባ በሃያ አራተኛው ቀን የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር በነቢዩ ሐጌ አማካይነት እንዲህ ሲል ተናገረ፤


በዚያው ወር በሃያ አራተኛው ቀን እግዚአብሔር እንደገና ለነቢዩ ለሐጌ ተናገረ።


ዳርዮስ የፋርስ ንጉሥ በሆነ በሁለተኛው ዓመት፥ በስምንተኛው ወር እግዚአብሔር በዒዶ የልጅ ልጅ በበራክዩ ልጅ በነቢዩ በዘካርያስ አማካይነት የተናገረው ቃል ይህ ነው፤


እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ፦


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios