Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ሮሜ 7:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 ታዲያ፥ ይህ መልካም የሆነው ነገር በእኔ ሞትን አመጣብኝ ማለት ነውን? አይደለም! ነገር ግን ኃጢአት፥ ኃጢአት ሆኖ እንዲገለጥ በመልካሙ ነገር አማካይነት ሞትን አመጣብኝ፤ ስለዚህ ኃጢአት በትእዛዝ አማካይነት የበለጠ ኃጢአተኛ ሆነ።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 ታዲያ በጎ የሆነው ነገር ሞት ሆነብኝን? ከቶ አይሆንም! ነገር ግን ኀጢአት በኀጢአትነቱ ይታወቅ ዘንድ በጎ በሆነው ነገር በኩል ሞትን አመጣብኝ፤ ይኸውም ኀጢአት በትእዛዝ በኩል ይብሱን ኀጢአት ይሆን ዘንድ ነው።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 እንግዲህ መልካም የሆነው ነገር ሞት ሆነብኝን? በጭራሽ! ነገር ግን ኃጢአት ኃጢአትነቱ እንዲታይ፥ መልካም በሆነው ነገር ሞትን ይሠራብኝ ነበር። ይኸውም ኃጢአት በትእዛዝ አማካይነት ያለ ልክ ኃጢአት እንዲሆን ነው።

Ver Capítulo Cópia de

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 እን​ግ​ዲህ ያ መል​ካም ነው ብዬ የማ​ስ​በው ነገር በውኑ አጥፊ ሆነኝ እላ​ለ​ሁን? አይ​ደ​ለም፤ ነገር ግን ኀጢ​አት ኀጢ​አት እንደ ሆነች በታ​ወ​ቀች ጊዜ ሞትን አበ​ዛ​ች​ብኝ፤ ከዚ​ያም ትእ​ዛዝ የተ​ነሣ ኀጢ​አ​ተ​ናው እን​ዲ​ታ​ወቅ፥ ኀጢ​አ​ትም ተለ​ይታ እን​ድ​ት​ታ​ወቅ ኦሪት መል​ካ​ሙን ከክፉ ልት​ለይ ተሠ​ር​ታ​ለች።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 እንግዲህ በጎ የሆነው ነገር ለእኔ ሞት ሆነብኝን? አይደለም፥ ነገር ግን ኃጢአት ሆነ፤ ኃጢአትም በትእዛዝ ምክንያት ያለ ልክ ኃጢአተኛ ይሆን ዘንድ፥ ኃጢአትም እንዲሆን ይገለጥ ዘንድ በጎ በሆነው ነገር ለእኔ ሞትን ይሠራ ነበር።

Ver Capítulo Cópia de




ሮሜ 7:13
7 Referências Cruzadas  

ከዚህ በኋላ ሴቶቹ በፍርሃትና በታላቅ ደስታ ከመቃብሩ በፍጥነት ሄዱ፤ ለደቀ መዛሙርቱም ሊነግሩ ሮጡ።


የወይኑ ተክል ባለቤት ራሱ ይመጣል፤ ገበሬዎቹንም ይገድላል፤ የወይኑንም አትክልት ለሌሎች ገበሬዎች ይሰጣል።” ሰዎቹም ይህን በሰሙ ጊዜ “ይህስ ከቶ አይሁን!” አሉ።


ኃጢአት ይበዛ ዘንድ ሕግ መጣ፤ ነገር ግን ኃጢአት በበዛ መጠን የእግዚአብሔር ጸጋ በይበልጥ በዛ።


ከሰው ባሕርይ ደካማነት የተነሣ ሕግ ሊያደርገው ያልቻለውን እግዚአብሔር አድርጎታል፤ የገዛ ልጁንም በኃጢአተኛ ሥጋ ምሳሌነት በኃጢአት ምክንያት ልኮ በሥጋው ኃጢአትን በፍርድ አስወገደ።


እንግዲህ ሕግ የእግዚአብሔርን የተስፋ ቃል ይቃወማልን? ከቶ አይቃወምም! ሕይወት የሚገኝበት ሕግ ተሰጥቶ ቢሆን ኖሮ ጽድቅ በሕግ አማካይነት በተገኘ ነበር።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios