48 ከብቶቻቸውን በበረዶ፥ በጎቻቸውንም በመብረቅ ገደለ።
48 ከብቶቻቸውን ለበረዶ፣ የከብት መንጋቸውን ለመብረቅ እሳት ዳረገ።
48 እንስሶቻቸውን ለበረዶ፥ ሀብታቸውንም ለመብረቅ ሰጠ።
አሁንም በመስክ የተሰማሩት እንስሶችህና በዚያ ያለው ንብረትህ ሁሉ ወደ መጠለያ እንዲጠጋ ትእዛዝ ስጥ፤ ወደ ቤት ያልገቡ ሰዎችም ሆኑ እንስሶች ቢኖሩ ግን በበረዶው ስለሚመቱ ሁሉም ያልቃሉ።’ ”
በረዶው በግብጽ ምድር ሁሉ በሜዳ የተገኘውን ማንኛውንም ነገር ሕዝቡንና እንስሶቹን ጭምር ጨፈጨፈ፤ በሜዳ ላይ ያለውን አትክልት ሁሉ መታ፤ ዛፎችንም ሁሉ ሰባበረ።
በረዶውና ነጐድጓዱ እጅግ ስለ በዛብን ወደ እግዚአብሔር ጸልዩልን፤ በእርግጥ እለቃችኋለሁ፤ ከእንግዲህ ወዲህ እዚህ የምትቈዩበት ጊዜ አይኖርም።”