Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




መዝሙር 77:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 ስለ እግዚአብሔር በማስብበት ጊዜ እተክዛለሁ፤ በጥሞና ሳሰላስል መንፈሴ ይዝላል።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 አምላክ ሆይ፤ አንተን ባሰብሁ ቍጥር ቃተትሁ፤ ባወጣሁ ባወረድሁም መጠን መንፈሴ ዛለች። ሴላ

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 በመከራዬ ቀን ጌታን ፈለግሁት፥ እጆቼ በሌሊት በፊቱ ናቸው፥ አላረፍሁምም፥ ነፍሴም መጽናናትን አልቻለችም።

Ver Capítulo Cópia de

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 የሰ​ማ​ነ​ው​ንና ያየ​ነ​ውን፥ አባ​ቶ​ቻ​ች​ንም የነ​ገ​ሩ​ንን፥ ለሚ​መጣ ትው​ልድ ከል​ጆ​ቻ​ቸው አል​ሰ​ወ​ሩም።

Ver Capítulo Cópia de




መዝሙር 77:3
21 Referências Cruzadas  

ወንዶችና ሴቶች ልጆቹ ሁሉ ሊያጽናኑት ወደ እርሱ መጡ፤ እርሱ ግን “ለልጄ እያለቀስሁ ወደ ሙታን ዓለም እወርዳለሁ” በማለት መጽናናትን እምቢ አለ። ስለዚህ ስለ ልጁ ማዘኑን ቀጠለ።


“በእኛ አማካይነት የሚነግርህ ከእግዚአብሔር የተሰጠህ መጽናናት አይበቃህምን?


የእግዚአብሔርን መቅሠፍት እፈራለሁ፤ ከግርማውም አስፈሪነት የተነሣ በፊቱ መቆም አልችልም።


ሁሉን የሚችል አምላክ በፍላጻዎቹ ወግቶኛል፤ መርዛቸውም በሰውነቴ ተሠራጭቶአል፤ የሚያስደነግጥ የእግዚአብሔር መቅሠፍት ዙሪያዬን ከቦኛል።


ከእንግዲህ ወዲህ ዝም አልልም! ከመንፈስ ጭንቀቴ የተነሣ እናገራለሁ፤ ከነፍሴ ምሬት የተነሣ አጒረመርማለሁ።


እኔ ለምን ተስፋ እቈርጣለሁ? ለምንስ እጨነቃለሁ። በእግዚአብሔር እተማመናለሁ ስለሚረዳኝም እርሱን አመሰግናለሁ።


እኔ ለምን ተስፋ እቈርጣለሁ፤ ለምንስ እጨነቃለሁ። በእግዚአብሔር እተማመናለሁ። ስለሚረዳኝም እርሱን አመሰግናለሁ።


እኔ ለምን ተስፋ እቈርጣለሁ? ለምንስ እጨነቃለሁ? በእግዚአብሔር እተማመናለሁ። ስለሚረዳኝም እርሱን አመሰግናለሁ።


መከራ በሚደርስብህ ጊዜ ጥራኝ፤ እኔም አድንሃለሁ፤ አንተም ታከብረኛለህ።”


ተስፋ ቈርጬ ሳለ ከሩቅ አገር ወደ አንተ እጮኻለሁ፤ ከእኔ በላይ ወደ አለው ከፍተኛ አምባ ምራኝ።


ሌሊቱን ሙሉ በአልጋዬ ላይ ሆኜ፥ ልቤ የምትወደውን ፈለግኹት፤ ፈለግኹት፤ ነገር ግን አላገኘሁትም።


አምላክ ሆይ! በችግራቸው ጊዜ ፈለጉህ በገሠጽካቸውም ጊዜ በጸሎት ወደ አንተ ተመለሱ።


አንተ በመከራ ጊዜ መሸሸጊያዬ ስለ ሆንክ አስደንጋጭ አትሁንብኝ፤


ሕይወቴ ሰላም እንዲያጣ ተደረገ፤ ደስታም ምን እንደ ሆነ ረሳሁ።


ሰው በሕይወቱ እያለ በኃጢአት ምክንያት ሲቀጣ የሚያጒረመርመው ለምንድን ነው?


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios