Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




መዝሙር 75:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ፍርድ የምሰጥበትን ጊዜ ወስኛለሁ፤ በዚያን ጊዜ በትክክል እፈርዳለሁ።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 አንተም እንዲህ አልህ፤ “ለይቼ በወሰንኋት ሰዓት፣ በቅን የምፈርድ እኔ ነኝ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 አቤቱ፥ እናመሰግንሃለን እናመሰግንሃለን፥ ስምህም ቅርብ ነው፥ ተኣምራትህን ሁሉ እንናገራለን።

Ver Capítulo Cópia de

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 በሀ​ገ​ሩም በሰ​ላም ኖረ፥ ማደ​ሪ​ያ​ውም በጽ​ዮን ነው፤

Ver Capítulo Cópia de




መዝሙር 75:2
12 Referências Cruzadas  

ከዚህ በኋላ የይሁዳ ሰዎች ወደ ኬብሮን መጡ፤ ዳዊትንም ቀብተው የይሁዳ ንጉሥ አደረጉት። ዳዊት ገለዓዳውያን የሆኑ የያቤሽ ሰዎች ሳኦልን እንደ ቀበሩት በሰማ ጊዜ፥


እንግዲህ የእስራኤል መሪዎች ሁሉ በኬብሮን ወደ ነበረው ወደ ዳዊት የመጡት በዚህ ዐይነት ነበር፤ እርሱም ከእነርሱ ጋር በእግዚአብሔር ፊት የቃል ኪዳን ስምምነት አደረገ፤ እነርሱም ቀብተው በእስራኤል ላይ አነገሡት።


በዚህ ዐይነት ዳዊት የመላው እስራኤል ንጉሥ ሆኖ ሕዝቡ ዘወትር ትክክለኛ ፍርድ ማግኘት እንዲችል ጥረት ያደርግ ነበር፤


ነቀፋ የሌለበት ሕይወት እኖራለሁ፤ ወደ እኔ የምትመጣው መቼ ነው? ከቤተሰቤ ጋር በቅንነት እኖራለሁ።


ለጽዮን ምሕረት የምታደርግላት ጊዜ ስለ ተቃረበና ጊዜውም አሁን ስለ ሆነ አንተ ትነሣለህ፤ ለእርስዋም ትራራለህ።


እኔም “ሁሉ ነገር የሚፈጸምበት ጊዜ ስላለው እግዚአብሔር በዐመፀኞችም ሆነ በቅኖች ላይ ይፈርዳል” ብዬ አሰብኩ።


አምላክ ሆይ! አንተ አምላኬ ነህ፤ ከፍ ከፍ አደርግሃለሁ፤ ስምህንም አመሰግናለሁ፤ አንተ እጅግ አስደናቂ የሆኑ ነገሮችን አድርገሃል፤ ከጥንት ጀምሮ ያቀድከውን ሁሉ፥ ፍጹምነት ባለው አስተማማኝ ሁኔታ አከናውነሃል።


ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፦ “የእኔ ጊዜ ገና አልደረሰም፤ የእናንተ ጊዜ ግን ዘወትር የተመቸ ነው።


ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰላቸው፦ “አብ በገዛ ሥልጣኑ የወሰነውን ጊዜና ዘመን እናንተ ልታውቁት አትችሉም።


እርሱ በመረጠው ሰው አማካይነት በዓለም ሁሉ ላይ በእውነት የሚፈርድበትን ቀን ወስኖአል፤ ይህንንም ለሁሉም ያረጋገጠው ያን የመረጠውን ሰው ከሞት በማስነሣቱ ነው።”


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios