Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




መዝሙር 68:25 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

25 ዘማሪዎች ከፊት፥ ሙዚቀኞች ከኋላ፥ አታሞ የሚመቱ ልጃገረዶች ከመካከል፥ ሆነው ይታያሉ።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

25 መዘምራን ከፊት፣ መሣሪያ የሚጫወቱ ከኋላ ሆነው ሲሄዱ፣ ከበሮ የሚመቱ ቈነጃጅትም በመካከላቸው ነበሩ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

25 አምላክ ሆይ ጉዞህን አዩት፥ የአምላኬና የንጉሤ ንግደት ወደ ቤተ መቅደስ።

Ver Capítulo Cópia de

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

25 ከተ​ማ​ቸው በረሃ ትሁን፥ በድ​ን​ኳ​ኖ​ቻ​ቸ​ውም የሚ​ቀ​መጥ አይ​ገኝ፤

Ver Capítulo Cópia de




መዝሙር 68:25
13 Referências Cruzadas  

ዳዊትና እስራኤላውያን ሁሉ መሰንቆና በገና እየደረደሩ፥ አታሞ እየመቱ፥ ጸናጽል እያንሿሹና እምቢልታ እየነፉ በመዘመር በሙሉ ኀይላቸው ለእግዚአብሔር ክብር ያሸበሽቡ ነበር።


ዘለዓለማዊው ፍቅርህ ከሕይወት እንኳ የሚሻል ስለ ሆነ አመሰግንሃለሁ።


ተአምራትን የምታደርግ አምላክ አንተ ነህ፤ አንተ በሕዝቦች መካከል ኀይልህን አሳይተሃል።


ዘማሪዎችና ጨፋሪዎች “የበረከታችን ሁሉ መገኛ ጽዮን ናት” እያሉ በደስታ ይዘምራሉ።


የአሮን እኅት ነቢይቱ ማርያም ከበሮዋን አነሣች፤ ሌሎችም ሴቶች ከበሮዎቻቸውን እየመቱና እየጨፈሩ ይከተሉአት ጀመር፤


ልጃገረዶቻቸውም በደስታ ይጨፍራሉ፤ ወንዶች ወጣቶችና ሽማግሌዎችም ደስ ይላቸዋል፤ አጽናናቸዋለሁ፤ ለቅሶአቸውን ወደ ደስታ፥ ሐዘናቸውንም ወደ ሐሴት እለውጣለሁ፤


ሕዝቤ እስራኤል ሆይ፥ እንደገና ትገነባላችሁ፤ ትገነቢአለሽም፥ እንደገና ከበሮ ትይዢአለሽ፤ ከሚደሰቱት ጋር አብረሽ በመውጣት ትጨፍሪአለሽ።


ዮፍታሔ በምጽጳ ወዳለው ቤቱ በተመለሰ ጊዜ ሴት ልጁ አታሞ ይዛ እየጨፈረች ልትቀበለው ወጣች፤ ያለ እርስዋም ሌላ ወንድ ወይም ሴት ልጅ አልነበረውም።


ዳዊት ጎልያድን ገድሎ ሲመለስና ወታደሮችም ወደየቤታቸው በማምራት ላይ ሳሉ፥ በእስራኤል በሚገኙት ከተሞች ሁሉ የሚኖሩ ሴቶች ሳኦልን ለመቀበል ወጡ፤ እነርሱም በእልልታ እየዘፈኑና እየጨፈሩ፥ የመስንቆ ድምፅ እያሰሙ አታሞ ይመቱ ነበር።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios