Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




መዝሙር 6:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 እግዚአብሔር ልመናዬን ያዳምጣል፤ እግዚአብሔር ለጸሎቴ መልስ ይሰጣል።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 እግዚአብሔር ልመናዬን ሰምቷል፤ እግዚአብሔር ጸሎቴን ይቀበላል።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 ዓመፃን የምታደርጉ ሁሉ፥ ከእኔ ራቁ፥ ጌታ የልቅሶዬን ቃል ሰምቶአልና።

Ver Capítulo Cópia de

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልመ​ና​ዬን ሰማኝ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸሎ​ቴን ተቀ​በለ።

Ver Capítulo Cópia de




መዝሙር 6:9
15 Referências Cruzadas  

እኔ ኢየሩሳሌምንና ሕዝብዋን እንዴት እንደምቀጣ በሰማህ ጊዜ፥ ራስህን አዋርደኽ በሐዘን ልብስህን በመቅደድና በማልቀስ ንስሓ ገብተሃል፤ ስለዚህ ጸሎትህን ሰምቼአለሁ።


በተጨነቅሁ ጊዜ ጩኸቴን ወደ እግዚአብሔር አሰማሁ፤ እርሱም ሰማኝ፤ ነጻም አወጣኝ።


መከራ በደረሰብኝ ጊዜ፥ ወደ እግዚአብሔር ጮኽኩ፤ እርሱም ሰማኝ።


በጠራሁህ ጊዜ ሰማኸኝ፤ በብርታትህም አበረታኸኝ።


ድምፄን ከፍ አድርጌ ወደ እግዚአብሔር እጮኻለሁ፤ እርሱም በተቀደሰ ተራራው ላይ ሆኖ ይሰማኛል።


ከድንጋጤዬ የተነሣ ከፊትህ ያራቅኸኝ መስሎኝ ነበር፤ ነገር ግን ርዳታህን ፈልጌ ለምሕረት ወደ አንተ ስጣራ ጩኸቴን ሰማህ።


“ወደ ሕዝቅያስ ሄደህ እንዲህ በለው፤ ‘እነሆ፥ የቀድሞ አባትህ የዳዊት አምላክ እኔ እግዚአብሔር ጸሎትህን ሰምቼአለሁ፤ እንባህንም አይቼአለሁ፤ ስለዚህም በዕድሜህ ላይ ዐሥራ አምስት ዓመት ጨምሬልሃለሁ፤


ጆሮህን ወደ እኔ መልስ፤ ለእርዳታም ድረስልኝ” የሚለውን ልመናዬን ሰምተሃል፤ ስለዚህ ዕረፍትን ስጠኝ።


“እግዚአብሔር ሆይ! ተጨንቄ ሳለሁ ወደ አንተ ተጣራሁ፤ አንተም መለስክልኝ፤ ርዳታህን ለማግኘት ጥልቅ ከሆነው ከሙታን ዓለም ወደ አንተ ጮኽኩ፤ አንተም ሰማኸኝ።


ሕይወቴ እየተዳከመ በሄደ ጊዜ እግዚአብሔርን አስታወስኩ፤ ወደ አንተ ወደ አምላኬ ጸለይኩ፤ ጸሎቴም ወደ ቤተ መቅደስህ ወደ አንተ መጣ።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios