Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




መዝሙር 42:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 ጠላቶቼ “ሁልጊዜ አምላክህ የት አለ?” ብለው በሚያላግጡብኝ ጊዜ አጥንቶቼ እንኳ ይታመማሉ።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 ጠላቶቼ ቀኑን ሙሉ፣ “አምላክህ የት አለ?” እያሉ፣ በነገር ጠዘጠዙኝ፣ ዐጥንቴም ደቀቀ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 እግዚአብሔርን፦ አንተ መጠጊያዬ ነህ፥ ለምን ረሳኸኝ? ጠላቶቼ ሲያስጨንቁኝ ለምን አዝኜ እመላለሳለሁ? እለዋለሁ።

Ver Capítulo Cópia de




መዝሙር 42:10
8 Referências Cruzadas  

ቀንና ሌሊት ስለ ማልቅስ እንባዬ እንደ ምግብ ሆኖኛል፤ ጠላቶቼ “አምላክህ የት አለ?” እያሉ ዘወትር ይጠይቁኛል።


አንተ አምላኬ፥ ጠንካራ ምሽጌ ነህ፤ ታዲያ፥ ስለምን ትተወኛለህ? ለምንስ ጠላቶቼ እያበሳጩ ያሳዝኑኝ?


ልቤ በውስጤ አስጨንቆኛል፤ የሞት ፍርሀትም ወደቀብኝ።


ያለ ጥንቃቄ የተነገረ ቃል እንደ ሰይፍ ያቈስላል፤ በጥበብ የተነገረ ቃል ግን ይፈውሳል።


ታዲያ፥ ለምን በፍጹም ዝም አልከን? ለምንስ ይህን ያኽል ጊዜ ተውከን?


እግዚአብሔርን የሚያገለግሉ ካህናት፥ በመሠዊያውና በመተላለፊያው መካከል ሆነው ያልቅሱ፤ “ጌታ ሆይ! ለሕዝብህ ራራ፤ አሕዛብ አምላካችሁ የት አለ? በማለት እንዲንቁንና እንዲዘባበቱብን አታድርግ” ይበሉ።


ጠላቴም ይህን ሁሉ ያያል፤ “አምላክህ እግዚአብሔር የት አለ?” ይለኝ የነበረው ጠላቴ ኀፍረትን ይከናነባል፤ እኔ የጠላቴን ውድቀት አያለሁ፤ በመንገድ ዳር እንዳለ ጭቃ ሲረገጥም እመለከታለሁ።


በዚህም በብዙዎች ልብ ያለው ስውር ሐሳብ ይገለጣል፤ የአንቺንም ልብ የሐዘን ሰይፍ ሰንጥቆት ያልፋል።”


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios