Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




መዝሙር 26:12 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 እግሮቼ በተስተካከለ ምድር ላይ ቆመዋል፤ እግዚአብሔርንም በጉባኤው ሁሉ ፊት አመሰግነዋለሁ።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 እግሮቼ በደልዳላ ስፍራ ቆመዋል፤ በታላቅ ጉባኤ መካከልም እግዚአብሔርን እባርከዋለሁ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 እግሮቼ በቅንነት ቆመዋልና፥ አቤቱ፥ በማኅበር አመሰግንሃለሁ።

Ver Capítulo Cópia de

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 ለሚ​ያ​ስ​ጨ​ን​ቁኝ ፈቃድ አት​ስ​ጠኝ፥ የዐ​መፅ ምስ​ክ​ሮች ተነ​ሥ​ተ​ው​ብ​ኛ​ልና፥ ሐሰ​ትም የዐ​መፅ ራስ ነው።

Ver Capítulo Cópia de




መዝሙር 26:12
11 Referências Cruzadas  

በሕዝብ ጉባኤ መካከል ታላቅነቱንም ያብሥሩ፤ በሽማግሌዎች ሸንጎ ያመስግኑት።


እግዚአብሔር ይመስገን! በቅኖች ሸንጎና በጉባኤም መካከል እግዚአብሔርን በሙሉ ልቤ አመሰግናለሁ።


በትእዛዙ መሠረት ለእግዚአብሔር ምስጋና ለማቅረብ የእስራኤል ነገዶች ሁሉ የሚሰበሰቡት ወደዚህች ከተማ ነው።


የምስጋና መዝሙር እየዘመርኩ፥ የአንተን ድንቅ ሥራዎች ሁሉ እናገራለሁ።


እግዚአብሔር ሆይ! የምመራበትን መንገድ አስተምረኝ፤ በጠላቶቼም ምክንያት በተደላደለ መንገድ ምራኝ።


ከረግረግ ቦታና ጭቃማ ከሆነው ከሚያዳልጥ ጒድጓድ አወጣኝ፤ እግሮቼን በአለት ድንጋይ ላይ አድርጎ የምቆምበትን ጠንካራ ቦታ ሰጠኝ።


በመጀመሪያ በቊጥር ትንሽ የሆነው የብንያም ነገድ ታየ፤ ቀጥሎም የይሁዳ መሪዎች ከነጭፍሮቻቸው ታዩ። በመጨረሻም የዛብሎንና የንፍታሌም መሪዎች ተከተሉ።


በሁሉም ነገር ታማኝ ሰው ያለ ስጋት ይኖራል። የጠማማ ሰው እርምጃ ግን ይጋለጣል።


ስለዚህም በቅዱሳት መጻሕፍት “ስምህን ለወንድሞቼ አበሥራለሁ፤ በማኅበርም መካከል በዜማ አመሰግንሃለሁ” ይላል፤


“ሰው ድልን የሚያገኘው በኀይሉ ስላልሆነ እግዚአብሔር የታማኞቹን እርምጃዎች ይጠብቃል፤ ክፉዎች ግን ወደ ጨለማ ይጣላሉ።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios