Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




መዝሙር 22:23 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

23 እናንተ እግዚአብሔርን የምትፈሩት አመስግኑት! እናንተ የያዕቆብ ዘሮች ሁሉ አክብሩት! እናንተ የእስራኤል ዘሮች ሁሉ በፍርሃት ከፍ ከፍ አድርጉት!

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

23 እናንተ እግዚአብሔርን የምትፈሩ፤ አወድሱት፤ እናንተ የያዕቆብ ዘር ሁላችሁ፤ አክብሩት፤ የእስራኤልም ዘር ሁላችሁ፤ እርሱን ፍሩት።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

23 ስምህን ለወንድሞቼ እነግራቸዋለሁ፥ በጉባኤም መካከል አመሰግንሃለሁ።

Ver Capítulo Cópia de




መዝሙር 22:23
22 Referências Cruzadas  

በአንተ ከሚመኩት ወገኖችህ እንደ አንዱ ሆኜ፥ ሕዝቦችህ ሲበለጽጉ እንዳይና የወገኖችህንም ደስታ እንድካፈል አድርገኝ።


ድምፄን ከፍ አድርጌ ለእግዚአብሔር ክብር እሰጣለሁ፤ በሕዝብ ጉባኤ መካከል አመሰግነዋለሁ።


እግዚአብሔር ይመስገን! በቅኖች ሸንጎና በጉባኤም መካከል እግዚአብሔርን በሙሉ ልቤ አመሰግናለሁ።


እናንተ የምትፈሩት ሁሉ የሚረዳችሁና የሚጠብቃችሁ እርሱ ስለ ሆነ በእግዚአብሔር ታመኑ።


የሚፈሩትን ሁሉ፥ ታላላቆችንም ሆነ ታናናሾችን ይባርካል።


በአክብሮት ለሚፈሩት የሚያስፈልጋቸውን ነገር ሁሉ ይሰጣቸዋል፤ ጩኸታቸውንም ሰምቶ ያድናቸዋል።


መጪው ትውልድ ያገለግለዋል፤ የወደፊት ትውልድም ስለ እግዚአብሔር ይነገረዋል።


እግሮቼ በተስተካከለ ምድር ላይ ቆመዋል፤ እግዚአብሔርንም በጉባኤው ሁሉ ፊት አመሰግነዋለሁ።


በምድርም የምትኖሩ ሁሉ እግዚአብሔርን ፍሩ፤ የዓለም ሕዝቦች ሁሉ እግዚአብሔርን አክብሩ።


በዚያን ጊዜ በሕዝብ ጉባኤ መካከል ሆኜ አመሰግንሃለሁ፤ ብዙ ሕዝብም በተሰበሰበበት ቦታ አከብርሃለሁ።


የምስጋና መሥዋዕት የሚያቀርብልኝ ያከብረኛል፤ መንገዴን ለሚከተል አዳኝነቴን አሳየዋለሁ።”


ጌታ አምላኬ ሆይ! በሙሉ ልቤ አመሰግንሃለሁ፤ ስምህንም ለዘለዓለም አከብራለሁ።


የታላላቅ መንግሥታት ሕዝቦች ያከብሩሃል፤ በጨካኞች መንግሥታት ከተሞች የሚኖሩ ሁሉ ይፈሩሃል።


እግዚአብሔር ለሚፈሩት ሰዎች ሁሉ ከትውልድ እስከ ትውልድ ምሕረቱን ያደርጋል።


እረኞቹ፥ ሁሉ ነገር መልአኩ እንዳላቸው ሆኖ በማየታቸውና በመስማታቸው፥ እግዚአብሔርን እያከበሩና እያመሰገኑ፥ ወደ ስፍራቸው ተመለሱ።


እንግዲህ ስትበሉም ሆነ ስትጠጡ ወይም ማናቸውንም ነገር ስታደርጉ ሁሉንም ነገር ለእግዚአብሔር ክብር አድርጉ።


ጌታ ሆይ! አንተን የማይፈራና ስምህንም የማያከብር ማን ነው? አንተ ብቻ ቅዱስ ነህ፤ የእውነት ፍርድህ ስለ ተገለጠ፥ ሕዝቦች ሁሉ መጥተው በፊትህ ይሰግዳሉ።”


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios