Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




መዝሙር 18:49 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

49 እግዚአብሔር ሆይ! ስለዚህ በሕዝቦች መካከል አመሰግንሃለሁ፤ ለስምህም እዘምራለሁ።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

49 ስለዚህ እግዚአብሔር ሆይ፤ በአሕዛብ መካከል አመሰግንሃለሁ፤ ስምህንም በመዝሙር እወድሳለሁ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

49 ከጠላቶቼ የሚታደገኝ እርሱ ነው፥ በእኔም ላይ ከቆሙት በላይ ታደርገኛለህ፥ ከግፈኛ ሰው ታድነኛለህ።

Ver Capítulo Cópia de




መዝሙር 18:49
11 Referências Cruzadas  

አምላኬ ሆይ! ልቤ ጽኑ ነው፤ ነቅቼ በሁለንተናዬ እዘምራለሁ፤ በዜማ አመሰግንሃለሁ።


እግዚአብሔር ሆይ! በመንግሥታት መካከል አመሰግንሃለሁ፤ በአሕዛብ መካከል የምስጋና መዝሙር አቀርብልሃለሁ።


እግዚአብሔር ሆይ! የቃልህን ተስፋ ስለ ሰሙ የዓለም ነገሥታት ሁሉ ያመሰግኑሃል።


ምነው መዳን ለእስራኤል ከጽዮን በመጣ! እግዚአብሔር የሕዝቡን ምርኮ በሚመልስበት ጊዜ፤ የያዕቆብ ልጆች ይደሰታሉ፤ የእስራኤል ሕዝብ ሐሴት ያደርጋሉ።


ስለዚህ ዝም አልልም፤ ለአንተ የምስጋና መዝሙር አቀርባለሁ፤ እግዚአብሔር ሆይ! አንተ አምላኬ ነህ፤ ስለዚህ ለዘለዓለም አመሰግንሃለሁ።


እግዚአብሔር ሆይ! በመንግሥታት መካከል አመሰግንሃለሁ፤ በአሕዛብም መካከል የምስጋና መዝሙር አቀርብልሃለሁ።


ከዚህ በኋላ መዝሙር ዘምረው ወደ ደብረ ዘይት ተራራ ወጡ።


ክርስቶስ የአይሁድ አገልጋይ የሆነበትም ሌላው ምክንያት አሕዛብ እግዚአብሔርን ስለ ምሕረቱ እንዲያመሰግኑት ነው፤ ይህም፦ “ስለዚህ በአሕዛብ መካከል አመሰግንሃለሁ፤ ለስምህም በዝማሬ ምስጋና አቀርባለሁ” ተብሎ እንደ ተጻፈው ነው።


ለሁሉ ነገር ሕይወት በሚሰጠው በእግዚአብሔርና በጴንጤናዊው ጲላጦስ ፊት በመልካም መታመን በመሰከረው በኢየሱስ ክርስቶስ ፊት አዝሃለሁ።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios