Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




መዝሙር 143:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 እግዚአብሔር ሆይ! ጸሎቴን ስማ! ለምሕረት የማደርገውን ልመና አድምጥ! በታማኝነትህና በእውነተኛነትህ ለጸሎቴ መልስ ስጠኝ!

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 እግዚአብሔር ሆይ፤ ጸሎቴን ስማ፤ ልመናዬን አድምጥ፤ በታማኝነትህና በጽድቅህም፣ ሰምተህ መልስልኝ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 ልጁ ባሳደደው ጊዜ፥ የዳዊት መዝሙር። አቤቱ፥ ጸሎቴን ስማ፥ ልመናዬን አድምጥ፥ በታማኝነትህ፥ በጽድቅህም መልስልኝ።

Ver Capítulo Cópia de

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 ለእ​ጆቼ ጠብን፥ ለጣ​ቶ​ቼም ሰል​ፍን ያስ​ተ​ማ​ራ​ቸው አም​ላኬ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይመ​ስ​ገን፤

Ver Capítulo Cópia de




መዝሙር 143:1
8 Referências Cruzadas  

“አሁንም እግዚአብሔር አምላክ ሆይ፥ ስለ እኔና ስለ ዘሮቼ የተናገርከውን የተስፋ ቃል ሁሉ ለዘለዓለም ፈጽም፤ ስምህ ለዘለዓለም ታላቅ ይሆን ዘንድ የተናገርከውን ፈጽም፤ ሰዎችም ልዑል እግዚአብሔር የእስራኤል አምላክ ነው ይላሉ። የባሪያህም የዳዊት ቤት በፊትህ የጸና ይሆናል።


እግዚአብሔርን “አንተ አምላኬ ነህ” እለዋለሁ፤ እግዚአብሔር ሆይ! ምሕረትህን ለማግኘት ስጸልይ ስማኝ!


እግዚአብሔር ሆይ! ትክክለኛ ፍርድ ለማግኘት የማቀርብልህን ጸሎት ስማ፤ ጩኸቴንም አድምጥ፤ በሽንገላ ሳይሆን በእውነት የማቀርበውን ጸሎት ስማ።


እግዚአብሔር ሆይ! መጠጊያ እንድትሆነኝ ወደ አንተ መጥቻለሁ፤ ስለዚህ እንዳፍር አታድርገኝ፤ በጽድቅህም አድነኝ።


በጽድቅህ ከችግር እንዳመልጥ አድርገህ አውጣኝ አድምጠህም አድነኝ።


ጌታ ሆይ! ስለ ፈጸምካቸው የጽድቅ ሥራዎች ሁሉ ብለህ ከተቀደሰችው ተራራህ ከኢየሩሳሌም ቊጣህንና መዓትህን እንድታነሣ እንለምንሃለን፤ በኃጢአታችንና በአባቶቻችንም በደል ምክንያት ኢየሩሳሌምና ሕዝብህ በጐረቤቶቻችን ሁሉ መካከል ተዋርደዋል።


ኃጢአታችንን ለእግዚአብሔር ብንናዘዝ እርሱ ታማኝና ጻድቅ ስለ ሆነ ኃጢአታችንን ሁሉ ይቅር ይልልናል፤ ከበደላችንም ሁሉ ያነጻናል።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios