Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




መዝሙር 140:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 ኀያሉ አዳኜ ጌታዬ እግዚአብሔር ሆይ! በጦርነት ቀን ራሴን እንደ ጋሻ ሸፍንልኝ።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 ብርቱ አዳኝ የሆንህ ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፤ በጦርነት ዕለት የራስ ቍር ሆንኸኝ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 ጌታንም፦ አንተ አምላኬ ነህ፥ የልመናዬን ቃል፥ አቤቱ፥ አድምጥ አልሁት።

Ver Capítulo Cópia de

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 እንደ ጓል በም​ድር ላይ ተሰ​ነ​ጣ​ጠቁ እን​ዲሁ አጥ​ን​ቶ​ቻ​ቸው በሲ​ኦል ተበ​ተኑ፥

Ver Capítulo Cópia de




መዝሙር 140:7
17 Referências Cruzadas  

በመላው ኤዶም ብዙ የጦር ሰፈሮችን አቋቋመ፤ በዚያም የሚኖሩ ሰዎች የእርሱ ተገዢዎች ሆኑ፤ እግዚአብሔር ዳዊትን በሄደበት ስፍራ ሁሉ ድልን ሰጠው።


ከዚያም በኋላ በግዛታቸው ውስጥ የጦር ሰፈሮችን አቋቋመ፤ ሶርያውያንም ለእርሱ ተገዢዎች ሆነው ገበሩለት፤ እግዚአብሔርም ዳዊትን በሄደበት ስፍራ ሁሉ ድልን እንዲቀዳጅ አደረገው።


አንተ ለነገሥታት ድልን ታጐናጽፋለህ፤ አገልጋይህን ዳዊትንም ከስለታም ሰይፍ ትታደገዋለህ።


የማዳን ጋሻህን ሰጠኸኝ፤ ቀኝ እጅህም ይጠብቀኛል፤ እኔን ለመርዳት መጥተህ ታላቅ አደረግኸኝ።


እግዚአብሔር ብርሃኔና ደኅንነቴ ስለ ሆነ ማንንም አልፈራም እግዚአብሔር የሕይወቴ ከለላ ስለ ሆነ የሚያስፈራኝ ማነው?


እኔ ሁልጊዜ በአንተ እጅ ነኝ፤ ከጠላቶቼ እጅና ከሚያሳድዱኝ ሁሉ አድነኝ።


አምላክ ሆይ! አንተ ብርታቴ ነህ፤ አንተ መጠጊያዬ ነህ፤ ዘለዓለማዊ ፍቅርህንም ታሳየኛለህ፤ ስለዚህ የምስጋና መዝሙር አቀርብልሃለሁ።


ያለ እርሱ የሚጠብቀኝና የሚያድነኝ የለም፤ መከላከያዬም እርሱ ስለ ሆነ ከቶ አልናወጥም።


መዳኔና ክብሬ የተገኘው ከእግዚአብሔር ነው፤ እርሱ የመጠጊያዬ አምባና መጠለያዬ ነው።


እርሱም ‘አንተ አባቴና አምላኬ ነህ፤ አንተ አምባዬና አዳኜ ነህ’ ይለኛል።


ኑ፤ እግዚአብሔርን በመዝሙር እናመስግን! ለመዳናችን አምባም የድል እልልታ እናስተጋባለት!


በእርግጥ እግዚአብሔር መድኃኒቴ ነው፤ በእርሱ ስለምተማመን የሚያስፈራኝ የለም፤ እግዚአብሔር አምላክ ኀይሌና ብርታቴ ነው፤ እርሱም መድኃኒቴ ሆኖአል።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios