Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




መዝሙር 139:14 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 በሚያስፈራና በሚያስገርም ሁኔታ ስለ ተፈጠርኩ አመሰግንሃለሁ፤ ሥራዎችህ ሁሉ አስደናቂዎች መሆናቸውን ጠንቅቄም ዐውቃለሁ።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 ግሩምና ድንቅ ሆኜ ተፈጥሬአለሁና አመሰግንሃለሁ፤ ሥራህ ድንቅ ነው፤ ነፍሴም ይህን በውል ተረድታለች።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 ግሩምና ድንቅ ሆኜ ተፈጥሬአለሁና አመሰግንሃለሁ፥ ሥራህ ድንቅ ነው፥ ነፍሴም እጅግ ታውቀዋለች።

Ver Capítulo Cópia de




መዝሙር 139:14
8 Referências Cruzadas  

እርሱ የማይቈጠረውን ተአምራት፦ የማይመረመረውን ታላቅ ነገር ያደርጋል።


እግዚአብሔር ሆይ! አንተ ብዙ ነገሮችን ፈጥረሃል፤ ሁሉንም በጥበብ አድርገሃል፤ ምድር አንተ በፈጠርካቸው ነገሮች ተሞልታለች።


እግዚአብሔር ብዙ አስደናቂ ነገሮችን አድርጎአል፤ በእርሱ አስደናቂ ሥራዎች የሚደሰት ሁሉ ያስባቸዋል።


እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ! ብዙ አስደናቂ ነገሮችን አድርገህልናል፤ ከአንተ የሚወዳደር ማንም የለም፤ አንተ ለእኛ ያቀድክልንን መልካም ነገር ማንም ሊቈጥረው አይችልም፤ እኔ ስለ እነርሱ በዝርዝር ለመናገርና ለማውራት ብሞክር ቊጥራቸው እጅግ የበዛ ይሆንብኛል።


ይህ ነገር የማይገባው አላዋቂ ለሆነ ሰው ነው፤ ሞኝ ሰውም ቢሆን አይገባውም።


የእግዚአብሔርን አገልጋይ የሙሴን መዝሙርና የበጉን መዝሙር እንዲህ እያሉ ይዘምሩ ነበር፥ “ሁሉን የምትችል ጌታ አምላክ ሆይ! ሥራህ ታላቅና አስደናቂ ነው፤ የሕዝቦች ንጉሥ ሆይ! መንገድህ ትክክልና እውነት ነው፤


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios