Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




መዝሙር 12:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 እግዚአብሔር ሆይ! አንተ ሁልጊዜ ጠብቀን፤ ክፉ ከሆኑት ከዚህ ዘመን ሰዎች አድነን።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ ትጠብቀናለህ፤ ከዚህም ትውልድ ለዘላለም ትከልለናለህ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 በምድር ምድጃ ላይ እንደ ተፈተነ ሰባት ጊዜ እንደ ተጣራ ብር የጌታ ቃላት የነጹ ቃላት ናቸው።

Ver Capítulo Cópia de




መዝሙር 12:7
15 Referências Cruzadas  

በምድር ላይ ያለ ማንኛውም ሰብአዊ ፍጡር ሌሎችን ለማስፈራራት እንዳይችል፥ አንተ ለወላጅ አልባና ለተጨቈኑ ሰዎች ትከላከላለህ።


የተስፋ ቃልህ እጅግ የታመነ ነው፤ እኔም በጣም እወደዋለሁ።


ከቤትህ ወጥተህ ስትሄድና ወደ ቤትህም ስትመለስ ዛሬም ለዘለዓለሙ ይጠብቅሃል።


እርሱን የሚወዱትን ሁሉ ይጠብቃል፤ ክፉዎችን ግን ይደመስሳል።


አምላክ ሆይ! የምታመነው በአንተ ስለ ሆነ ጠብቀኝ፤


ከእግዚአብሔር በቀር ማነው አምላክ? ከእርሱስ በቀር መጠጊያ የሚሆን ማነው?


እግዚአብሔርን መፍራት ለዘለዓለም የሚኖር ንጽሕና ነው፤ የእግዚአብሔር ፍርዶች ሁሉ እያንዳንዳቸው እውነትና ጽድቅ ናቸው።


እግዚአብሔር ትክክለኛ ፍርድን ይወዳል፤ ታማኞቹንም አይተዋቸውም፤ ለዘለዓለምም ይጠብቃቸዋል፤ የክፉዎች ዘር ግን ይጠፋል።


እንዲጠብቃቸው በእርሱ ስለ ተማጸኑም ይረዳቸዋል፤ ያድናቸዋልም፤ ከክፉዎችም እጅ ይታደጋቸዋል።


እኔ እግዚአብሔር እጠብቀዋለሁ በየጊዜውም ውሃ አጠጣዋለሁ፤ ማንም ሰው እንዳይጐዳው ሌሊትና ቀን እጠብቀዋለሁ።


ነገር ግን፥ ዮሐንስ ከፈሪሳውያንና ከሰዱቃውያን ብዙዎች ለመጠመቅ ወደ እርሱ ሲመጡ ባየ ጊዜ፥ እንዲህ አላቸው፦ “እናንተ የእባብ ልጆች! ከሚመጣው ቊጣ እንድታመልጡ ማን አስጠነቀቃችሁ?


እግዚአብሔር በእውነት ሕዝቡን ይወዳል፤ ቅዱሳኑን ሁሉ ይጠብቃል፤ እነርሱም በእግሩ ሥር ተንበርክከው ይሰግዳሉ፤ መመሪያውንም ይቀበላሉ፤


እናንተም በመጨረሻው ቀን ለሚገለጠው መዳን በእምነት አማካይነት በእግዚአብሔር ኀይል ተጠብቃችኋል።


የኢየሱስ ክርስቶስ አገልጋይና የያዕቆብ ወንድም ከሆነው ከይሁዳ፥ ለተጠራችሁት፥ በእግዚአብሔር አብ ለተወደዳችሁት፥ በኢየሱስ ክርስቶስ ለተጠበቃችሁት ሁሉ፥


“ሰው ድልን የሚያገኘው በኀይሉ ስላልሆነ እግዚአብሔር የታማኞቹን እርምጃዎች ይጠብቃል፤ ክፉዎች ግን ወደ ጨለማ ይጣላሉ።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios