Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




መዝሙር 107:32 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

32 በሕዝብ ጉባኤ መካከል ታላቅነቱንም ያብሥሩ፤ በሽማግሌዎች ሸንጎ ያመስግኑት።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

32 በሕዝብ ጉባኤ መካከል ከፍ ከፍ ያድርጉት፤ በሽማግሌዎችም ሸንጎ ይወድሱት።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

32 በሕዝብ ጉባኤ መካከል ከፍ ከፍ ያድርጉት፥ በሽማግሌዎችም ሸንጎ ያመስግኑት።

Ver Capítulo Cópia de




መዝሙር 107:32
16 Referências Cruzadas  

እግዚአብሔር ይመስገን! በቅኖች ሸንጎና በጉባኤም መካከል እግዚአብሔርን በሙሉ ልቤ አመሰግናለሁ።


ትእዛዞችህን በነገሥታት ፊት እናገራለሁ፤ ከቶም አላፍርም።


እግዚአብሔር ሕያው ነው! አምላኬ መጠጊያዬ ይመስገን! ያዳነኝም ኀያል አምላክ ከፍ ከፍ ይበል።


የስምህን ታላቅነት ለወገኖቼ እናገራለሁ፤ እነርሱ በተሰበሰቡበት ስፍራ አመሰግንሃለሁ፤


ስለ ሠራኸው መልካም ሥራ ብዙ ሕዝብ በተሰበሰበበት ስፍራ አመሰግንሃለሁ፤ በሚፈሩህ ሰዎች ፊት ሆኜ፥ የተሳልኩትን ስለት እፈጽማለሁ።


እግሮቼ በተስተካከለ ምድር ላይ ቆመዋል፤ እግዚአብሔርንም በጉባኤው ሁሉ ፊት አመሰግነዋለሁ።


በዚያን ጊዜ በሕዝብ ጉባኤ መካከል ሆኜ አመሰግንሃለሁ፤ ብዙ ሕዝብም በተሰበሰበበት ቦታ አከብርሃለሁ።


ጸጥ ብላችሁ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ዕወቁ፤ በሕዝቦች መካከል ከፍ ከፍ እላለሁ፤ በምድርም ላይ ከፍ ከፍ እላለሁ።


እግዚአብሔር ያደረገልኝን ሁሉ እንድነግራችሁ፥ እግዚአብሔርን የምትፈሩ ሁሉ ኑ ስሙ።


አምላካችን እግዚአብሔርን አመስግኑት! በእግሩ ማረፊያ ሥር ስገዱ! እርሱ ቅዱስ ነው።


አምላካችን እግዚአብሔር ቅዱስ ነውና፥ እርሱን አክብሩት፤ በተቀደሰው ተራራም ላይ ስገዱለት፥


እግዚአብሔር በመዝሙር የማመሰግነው መከላከያ ኀይሌ ነው፤ ከጠላት እጅ ያዳነኝ ታዳጊዬም እርሱ ነው፤ እርሱ አምላኬ ስለ ሆነ አመሰግነዋለሁ፤ የአባቴም አምላክ ስለ ሆነ፥ ስለ ገናናነቱ እዘምራለሁ።


በዚያን ቀን እንዲህ ትላላችሁ፦ “እግዚአብሔርን አመስግኑ! ስሙንም አክብሩ! በሕዝቦች መካከል እርሱ ያደረገውን ተናገሩ! ስለ ገናናነቱም መስክሩ!


አምላክ ሆይ! አንተ አምላኬ ነህ፤ ከፍ ከፍ አደርግሃለሁ፤ ስምህንም አመሰግናለሁ፤ አንተ እጅግ አስደናቂ የሆኑ ነገሮችን አድርገሃል፤ ከጥንት ጀምሮ ያቀድከውን ሁሉ፥ ፍጹምነት ባለው አስተማማኝ ሁኔታ አከናውነሃል።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios