Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




መዝሙር 106:32 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

32 በመሪባ ምንጮች አጠገብ ሕዝቡ እግዚአብሔርን አስቈጡት፤ በእነርሱም ምክንያት ሙሴ ችግር ላይ ወደቀ።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

32 ደግሞም በመሪባ ውሃ አጠገብ እግዚአብሔርን አስቈጡት፤ ሙሴም ከእነርሱ የተነሣ ተቸገረ፤

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

32-33 በክርክር ውኃ ዘንድም አስቈጡት፥ መንፈሱን አስመርረዋታልና፥ በእነርሱም የተነሣ ሙሴ ተበሳጨ፥ በከንፈሮቹም ያለማስተዋል ተናገረ።

Ver Capítulo Cópia de

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

32 በአ​ሕ​ዛብ ጉባኤ ከፍ ከፍ ያደ​ር​ጉ​ታል፥ በሽ​ማ​ግ​ሌ​ዎ​ችም ሸንጎ ያመ​ሰ​ግ​ኑ​ታል።

Ver Capítulo Cópia de




መዝሙር 106:32
9 Referências Cruzadas  

በበረሓ ሳሉ ብዙ ጊዜ በእርሱ ላይ ዐመፁ፤ በምድረ በዳም ብዙ ጊዜ አሳዘኑት።


በመከራ ላይ በነበራችሁበት ጊዜ ጠራችሁኝ፤ እኔም አዳንኳችሁ፤ ከመሰወሪያ ስፍራዬ፥ ከሞገድ ውስጥ ሰማኋችሁ፤ በክርክር ምንጮች አጠገብ ፈተንኳችሁ።


እስራኤላውያን “እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው ወይስ አይደለም?” በማለት በማጒረምረማቸውና እግዚአብሔርን በመፈታተናቸው ያ ስፍራ ማሳህና እና መሪባ ተብሎ ተጠራ።


በእናንተው ምክንያት እግዚአብሔር በእኔም ላይ እንኳ ተቈጥቶ እንዲህ አለኝ፤ ‘ሙሴ፥ አንተም ራስህ እንኳ ወደዚያች ምድር አትገባም፤


“ነገር ግን በእናንተው በሕዝቡ ምክንያት እግዚአብሔር ተቈጣኝ፤ ልመናዬንም ማዳመጥ አልፈለገም፤ ይልቁንም በዚህ ፈንታ እንዲህ አለኝ፤ ‘እንግዲህስ በቃህ! ዳግመኛ ይህን ነገር አታንሣ!


በእናንተም ምክንያት እኔን ተቈጣ፤ የዮርዳኖስንም ወንዝ ተሻግሬ እንዳልሄድና እርሱ የሚሰጣችሁን ያቺን ለምለም ምድር እንዳላይ በመሐላ አስታወቀኝ።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios