Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




መዝሙር 104:21 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 እግዚአብሔር የሚያዘጋጀውን ምግብ ሲያድኑ የአንበሳ ደቦሎች ያገሣሉ።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 የአንበሳ ግልገሎች ምግብ ፍለጋ ይጮኻሉ፤ የሚበሉትንም ከእግዚአብሔር ይሻሉ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 የአንበሳ ግልገሎች ለመንጠቅ ይጮኻሉ፥ ከእግዚአብሔርም ምግባቸውን ይሻሉ።

Ver Capítulo Cópia de

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 የቤቱ ጌታም አደ​ረ​ገው፥ በገ​ን​ዘቡ ሁሉ ላይ ገዢ አደ​ረ​ገው፥

Ver Capítulo Cópia de




መዝሙር 104:21
11 Referências Cruzadas  

በጫካው ውስጥ ታጋድመውና አድብተው ሳሉ ለአንበሳይቱ አደን ታድናለህን?


ልጆችዋ ምግብ አጥተው ሲቅበዘበዙ ወደ እኔም ሲጮኹ ለቁራ ምግብ የሚሰጣት ማነው?”


ሁሉም በተስፋ ወደ አንተ ይመለከታሉ፤ አንተም በሚያስፈልጋቸው ጊዜ ምግባቸውን ትሰጣቸዋለህ።


ለእንስሶች ምግብን ይሰጣል፤ ምግብ አጥተው የሚጮኹ የቊራ ጫጩቶችንም ይመግባል።


የአንበሳ ደቦሎች ያጣሉ፤ ይራባሉም፤ እግዚአብሔርን የሚፈልጉት ግን ምንም አይጐድልባቸውም፤ መልካም ነገርም አያጡም።


እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ፦ “አንበሳ በገደለው እንስሳ ላይ በሚያገሣበት ጊዜ እረኞች ተጠራርተው የቱንም ያኽል ቢጮኹ የእነርሱ ጩኸት ምንም እንደማያስፈራው እኔም የሠራዊት አምላክ የጽዮንን ተራራና ኰረብቶቿን ለመከላከል የሚያግደኝ የለም።


የግጦሽ ሣር በማጣት ከብቶች ያላዝናሉ፤ የበጎች መንጋ ሳይቀሩ ተርበው በብርቱ ሥቃይ ላይ ይገኛሉ።


ወንዞች ስለ ደረቁባቸው፥ የሜዳውም ሣር ሁሉ ስለ ተቃጠለባቸው፥ የዱር አራዊት እንኳ ወደ አንተ ይጮኻሉ።


እናንተም የምድር እንስሶች አትፍሩ፤ የምትሰማሩባቸው መስኮች ለምልመዋል፤ ዛፎችም አፍርተዋል፤ የበለሱና የወይኑ ፍሬ እጅግ የበዛ ሆኖአል።


አንበሳ በደን ውስጥ ዐድኖ የሚበላውን ሳያገኝ በከንቱ ያገሣልን? የአንበሳ ደቦልስ አንዳች ነገር ዐድኖ ሳይዝ በሚኖርበት ቦታ ድምፁን ያሰማልን?


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios