Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ምሳሌ 31:31 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

31 እርስዋ ለምታደርገው ነገር ሁሉ አመስግኑአት፤ ስለ መልካም ሥራዋ በሰዎች ሁሉ ዘንድ ልትከበር ይገባታል።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

31 የሚገባትን ሽልማት ስጧት፤ ሥራዋም በየአደባባዩ ያስመስግናት።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

31 ከእጅዋ ፍሬ ስጡአት፥ ሥራዎችዋም በሸንጎ ያመስግኑአት።

Ver Capítulo Cópia de




ምሳሌ 31:31
17 Referências Cruzadas  

ሠርተህ የምታፈራውን ትመገባለህ፤ ደስታና ሀብትም ታገኛለህ።


የጻድቅ ሰው ሥራ የዘለዓለም ሕይወትን ያስገኛል፤ ዐመፅ ግን ለሕይወት መጥፋት ምክንያት ይሆናል።


ደኅና መሬት ፈልጋ ትገዛለች፤ ሠርታ በምታገኘውም ገንዘብ የወይን አትክልት ቦታ ታዘጋጃለች።


ቊንጅና ከንቱ ነው፤ ውበትም ይጠፋል፤ እግዚአብሔርን የምትፈራ ሴት ግን ልትመሰገን ይገባታል።


በኢየሩሳሌም ነግሦ የነበረ ጥበበኛው የዳዊት ልጅ የተናገረው የጥበብ ቃል ይህ ነው፤


እነርሱንም የምታውቁአቸው በሥራቸው ፍሬ ነው። ከእሾኽ ቊጥቋጦ የወይን ፍሬ፥ ከኮሸሽላስ የበለስ ፍሬ ይለቀማልን?


ስለዚህ፥ ሐሰተኞች ነቢያትን በሥራቸው ፍሬ ታውቁአቸዋላችሁ።


ስለዚህ ጴጥሮስ ተነሥቶ ከመልእክተኞቹ ጋር መጣ፤ በደረሰም ጊዜ በሰገነቱ ላይ ወዳለው ክፍል ወሰዱት፤ ባሎቻቸው የሞቱባቸው ሴቶች ሁሉ በዙሪያው ቆመው እያለቀሱ ዶርቃ ከእነርሱ ጋር በሕይወት ሳለች የሠራቻቸውን ቀሚሶችና ልብሶች ያሳዩት ነበር፤


በጌታ አገልግሎት ለሚደክሙት ለትሩፋይናና ለትሩፎሳ ሰላምታ አቅርቡልኝ። በጌታ አገልግሎት እጅግ ለደከመችውና በክርስቶስ ለምወዳት ለፔርሲስ ሰላምታ አቅርቡልኝ።


ለእናንተ ብዙ ለደከመችው ለማርያም ሰላምታ አቅርቡልኝ።


ይህንንም ስል የእናንተን ስጦታ ለማግኘት በመጓጓት ሳይሆን የልግሥናችሁ ፍሬ እንዲበዛላችሁ በመመኘት ነው።


እንዲሁም መልካም ሥራ ግልጥ ነው፤ ግልጥ ያልሆነውም እንኳ ተሰውሮ አይቀርም።


እግዚአብሔር ቅን ፈራጅ ነው፤ ስለዚህ ሥራችሁንና በፊትም ሆነ አሁን ቅዱሳንን በመርዳት ስለ ስሙ ያሳያችሁትን ፍቅር አይረሳም።


ከሰማይም እንዲህ የሚል ድምፅ ሰማሁ፤ ይህን ጻፍ፤ “ከእንግዲህ ወዲህ የጌታ ኢየሱስ ሆነው የሚሞቱ የተባረኩ ናቸው!” መንፈስ ቅዱስም “አዎ! ከድካማቸው እንዲያርፉ ሥራቸው ይከተላቸዋል” ይላል።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios