Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ምሳሌ 30:32 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

32 ሞኝነትህ ትምክሕተኛ እንድትሆን ቢያደርግህና ክፉ ነገር ለማድረግ ብታቅድ፥ ቆም ብለህ አስብ።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

32 “ተላላ ሆነህ ራስህን ከፍ ከፍ ካደረግህ፣ ወይም ክፉ ነገር ካቀድህ፣ እጅህን በአፍህ ላይ አድርግ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

32 ከፍ ከፍ በማለት የተሞኝህ እንደሆነ፥ ክፉም ያሰብህ እንደሆነ፥ እጅህን በአፍህ ላይ ጫን።

Ver Capítulo Cópia de




ምሳሌ 30:32
8 Referências Cruzadas  

እስቲ ወደ እኔ ተመልከቱ፤ መናገር እስኪያቅታችሁ ድረስ ሁኔታዬ ያሠቅቃችኋል።


“ጌታ ሆይ! እኔ ለምንም የማልጠቅም ከንቱ ሰው ነኝ፤ ከእንግዲህ ወዲህ አፌን በእጄ ይዤ ዝም ከማለት በስተቀር፥ ለአንተ የምሰጠው መልስ የለኝም።


ሞኝ ዝም ሲል ጥበበኛ ይመስላል፤ ምንም ሳይናገር ቢቀር እንደ ብልኅ ይቈጠራል።


በራሱ አስተሳሰብ ጠቢብ የሆነ ከሚመስለው ሰው ይልቅ ሞኝ ሰው ተስፋ አለው።


አውራ ፍየሎች፥ የሚንጐራደዱ አውራ ዶሮዎች፥ በሕዝቦቻቸው ፊት በክብር የሚታዩ ነገሥታት ናቸው።


የሕግ ትእዛዝ የሚመለከተው ከሕግ በታች ያሉትን እንደ ሆነ እናውቃለን፤ በዚህ ምክንያት ሰዎች የሚያመካኙት አጥተው ዝም ይላሉ፤ ዓለሙም ሁሉ በእግዚአብሔር ፍርድ ሥር ይሆናል።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios