Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ምሳሌ 30:19 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 እነርሱም፦ “በሰማይ የሚበር ንስር፥ በአለት ላይ የሚጐተት እባብ፥ በባሕር ላይ የሚጓዝ መርከብና ከሴት ጋር ፍቅር የያዘው ወንድ” ናቸው።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 የንስር መንገድ በሰማይ፣ የእባብ መንገድ በቋጥኝ፣ የመርከብ መንገድ በባሕር፣ የሰውም መንገድ ከሴት ልጅ ጋራ ናቸው።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 እነርሱም የንስር መንገድ በሰማይ፥ የእባብ መንገድ በድንጋይ ላይ፥ የመርከብ መንገድ በባሕር ላይ፥ የሰውም መንገድ ከቈንጆ ጋር ናቸው።

Ver Capítulo Cópia de




ምሳሌ 30:19
7 Referências Cruzadas  

ንስርን ወደ ላይ ወጥቶ በከፍተኛም ቦታ ላይ ጎጆውን የሚሠራው አንተ አዘኸው ነውን?


“አንድ ሰው አንዲት ልጃገረድን አታሎ ክብረ ንጽሕናዋን ቢደፍር ማጫ ሰጥቶ ያግባት፤


ላስተውላቸው የማልችል እጅግ ምሥጢር የሆኑ ሦስት ነገሮች አሉ፤ እንዲያውም አራት ናቸው።


በእግዚአብሔር ተማምነው የሚኖሩ ግን ኀይላቸው ይታደስላቸዋል። እንደ ንሥር በክንፍ ይበራሉ፤ ይሮጣሉ አይታክቱም፤ ይሄዳሉ አይደክሙም።


ክንፉን ዘርግቶ ወደ ታች እንደሚወረወር ንስር በሞአብ ላይ የሚያንዣብብ ጠላት መምጣቱን እግዚአብሔር ተናገረ፤


ጠላት በቦጽራ ላይ ክንፉን በስፋት ዘርግቶ ወደ ታች እንደሚወርድ ንስር በመሆን ጉብ ይልባታል፤ በዚያን ጊዜ የኤዶም ወታደሮች በምጥ ተይዛ በፍርሃት እንደምትጨነቅ ወላድ ሴት ይሆናሉ።


እግዚአብሔር ቋንቋቸውን የማታውቀውን የሕዝቦች ሠራዊትን ከሩቅ ምድር ያመጣብሃል፤ እነርሱም እንደ ንስር በአንተ ላይ ይወርዱብሃል፤


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios