Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ምሳሌ 29:12 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 አንድ መሪ ሐሰተኛ ወሬ የሚቀበል ከሆነ ባለሟሎቹ የሆኑ ባለሥልጣኖች ሁሉ ግፈኞች ይሆናሉ።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 ገዥ የሐሰት ወሬ የሚሰማ ከሆነ፣ ሹማምቱ ሁሉ ክፉዎች ይሆናሉ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 አስተዳዳሪ ለሐሰተኛ ነገር ትኩረት ቢሰጥ፥ ከእርሱ በታች ያሉት ሁሉ ዓመፀኞች ይሆናሉ።

Ver Capítulo Cópia de




ምሳሌ 29:12
15 Referências Cruzadas  

ሚስቱ “የአንተ አገልጋይ እንዲህ አደረገኝ” ብላ የነገረችውን ታሪክ በሰማ ጊዜ የዮሴፍ አሳዳሪ እጅግ ተቈጣ።


ወጣቶቹም በሰጡት ምክር መሠረት “አባቴ በእናንተ ላይ ከባድ የአገዛዝ ቀንበር ጭኖባችሁ ነበር፤ እኔ ደግሞ ይኸው የአገዛዝ ቀንበር ይበልጥ እንዲከብድባችሁ አደርጋለሁ፤ አባቴ በአለንጋ ይገርፋችሁ ነበር፤ እኔ ግን እንደ ጊንጥ በሚናደፍ ጅራፍ በመግረፍ አሠቃያችኋለሁ!” ሲል መለሰላቸው።


የይሁዳ ሰዎች ግን ለእግዚአብሔር ቃል ታዛዦች ሆነው አልተገኙም፤ ይልቁንም ምናሴ እስራኤላውያን ወደፊት እየገፉ ሲመጡ እግዚአብሔር ከፊታቸው ነቃቅሎ ያጠፋላቸው ሕዝቦች ይፈጽሙት ከነበረው ይበልጥ ወደ ከፋ ኃጢአት መራቸው።


በፍርድ ዙፋን ላይ የተቀመጠ ንጉሥ ክፉ የሆነውን ነገር ሁሉ አበጥሮ የሚያውቅ ዐይን አለው።


የሰሜን ነፋስ ዝናብን እንደሚያመጣ ሐሜትም ቊጣን ማስከተሉ የተረጋገጠ ነው።


ሴዴቅያስም ሆነ መኳንንቱ ወይም ሕዝቡ እግዚአብሔር በነቢዩ በኤርምያስ አማካይነት ለተናገረው ቃል ታዛዦች አልሆኑም።


ባለሟሎቹንም ጠርቶ “ንጉሡ በአንተ ተደስቶአል፤ የእርሱ ባለሟሎች የሆኑት ባለሥልጣኖቹም ይወዱሃል፤ ስለዚህ የእርሱን ልጅ ታገባ ዘንድ አሁን ጥሩ ጊዜ ገጥሞሃል” ብለው ለዳዊት በግል እንዲነግሩት አዘዘ።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios